አምላክ ሆይ! አዲስ መዝሙር እቀኝልሃለሁ፤ ዐሥር አውታር ያለው በገናም በመደርደር እዘምርልሃለሁ።
አምላክ ሆይ፤ አዲስ ቅኔ እቀኝልሃለሁ፤ ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ።
አቤቱ፥ አዲስ ቅኔ እቀኛልሃለሁ፥ ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ።
እግዚአብሔር ለሚታገሡት ቸር ነው። ይቅርታውም በሥራው ሁሉ ላይ ነው።
እግዚአብሔርን አመስግኑ! ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! በምእመናን ጉባኤ አመስግኑት!
በአንደበቴ አዲስ መዝሙር፥ እርሱም ለአምላካችን የምስጋና መዝሙር አኖረ፤ ብዙዎች በፍርሃት ተመልክተው በእግዚአብሔርም ይታመናሉ።
ድንቅ ነገሮችን ስላደረገና፥ በኀያል ሥልጣኑ ድልን ስለ ተጐናጸፈ፥ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩለት!
በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች፥ በሽማግሌዎችም ፊት መቶ አርባ አራቱ ሺህ ሰዎች አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ ይህን መዝሙር ከምድር ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራቱ ሺህ ሰዎች በቀር ማንም ሊማረው አልቻለም።