የመብረቅ ብልጭታን ልከህ ጠላቶችህን በትናቸው፤ ፍላጻዎችህንም በመወርወር አሳዳቸው።
የመብረቅ ብልጭታ ልከህ በትናቸው፤ ፍላጻህን ሰድደህ ግራ አጋባቸው።
መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው በትናቸውም፥ ፍላጾችህን ላካቸው አስደንግጣቸውም።
“ኀይልህ ግሩም ነው” ይላሉ፥ ግርማህንም ይነጋገራሉ፥ ብርታትህንም ያስረዳሉ።
እግዚአብሔር ሆይ! ጠላቶችህን በገሠጽህ ጊዜ፥ የቊጣ ድምፅህንም ባሰማህ ጊዜ የውቅያኖስ ወለል ታየ፤ የምድርም መሠረት ተጋለጠ።
ፍላጻዎችህን በእነርሱ ላይ ታነጣጥራለህ፤ ወደ ኋላም ተመልሰው እንዲሸሹ ታደርጋለህ።
ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፤ የጠላቶችህንም ልብ ይወጋሉ፤ መንግሥታትም ተሸንፈው በእግርህ ሥር ይወድቃሉ።
እግዚአብሔር ንግግራቸው በራሳቸው ላይ ተመልሶ እንዲወድቁ ያደርጋቸዋል። የሚያዩአቸው ሁሉ በፍርሃት ከእነርሱ ይሸሻሉ።
“ተከታታይ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤ ፍላጻዎቼን ሁሉ በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ።
ከተገደሉትና ከተማረኩት ከጠላት መሪዎችም ራስ ደም ፍላጻዎቼን አሰክራለሁ፤ ሰይፌ የጠላትን ሥጋ ይቈራርጣል።’