መዝሙር 143:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! መንፈሴ ስለ ዛለብኝ ፈጥነህ መልስ ስጠኝ! ፊትህን ከእኔ አትሰውርብኝ! አለበለዚያ ወደ ጥልቁ ጒድጓድ እንደሚወርዱት ሰዎች እሆናለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈጥነህ መልስልኝ፤ መንፈሴ ደከመች፤ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እንዳልሆን፣ ፊትህን ከእኔ አትሰውር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፥ መንፈሴ ዛለ፥ ፊትህን ከኔ አትሰውር፥ ወደ ጉድጓድም እንደሚወርዱ እንዳልሆን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጅህን ከአርያም ላክ፥ ከብዙ ውኃም አድነኝ፤ ከባዕድ ልጆችም እጅ፥ |
አምላኬና አዳኜ ሆይ! ፊትህን ከእኔ አትሰውርብኝ፤ ተቈጥተህም እኔን አገልጋይህን ከአንተ እንድርቅ አታድርገኝ፤ ረዳቴም ስለ ሆንክ ከእኔ አትለይ፤ አትተወኝም።
ከሙታን ዓለም ሊያመሰግንህ የሚችል አንድ እንኳ የለም፤ ሙታንም ሊያመሰግኑህ አይችሉም፤ ወደ መቃብር የወረዱትም ታማኝነትህን ተስፋ አያደርጉም።