መዝሙር 143:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጆቼን ለጸሎት ወደ አንተ እዘረጋለሁ፤ ደረቅ ምድር ውሃ እንደሚያስፈልገው እንዲሁም ነፍሴ አንተን ተጠማች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፥ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው፥ በትናቸውም፤ ፍላጾችህን ላካቸው፥ አስደንግጣቸውም። |
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ለማግኘት በብርቱ እናፍቃለሁ፤ ሁለንተናዬ አንተን ይመኛል፤ ውሃ በማጣት ደርቆ እንደ ተሰነጣጠቀ መሬት ነፍሴ አንተን ተጠማች።
ሙሴም ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “ከከተማው እንደ ወጣሁ እጄን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነጐድጓዱም ይቆማል፤ በረዶም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም፤ በዚህ ዐይነት አንተም ምድር የእግዚአብሔር እንደ ሆነች ታውቃለህ።
የሚያቃጥለው አሸዋ ኩሬ ይሆናል፤ ደረቁም ምድር በምንጭ ውሃ ይረሰርሳል፤ የቀበሮዎች መፈንጫ የነበረው ስፍራ ለምለም ሣርና ቄጠማ የሚበቅልበት ይሆናል።