ከዚህ በኋላ አብራም ሎጥን እንዲህ አለው፤ “እኛ ወንድማማች ስለ ሆንን በእኔና በአንተ መካከል እንዲሁም በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ጠብ ሊነሣ አይገባም፤
መዝሙር 133:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድማማች አብረው ይኖሩ ዘንድ ምንኛ መልካምና ደስ የሚያሰኝ ነው! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ሲኖሩ፣ እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊት የዕርገት መዝሙር። ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ እንዴት መልካም፥ እንዴት ውብ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ቤት፥ በአምላካችን ቤት አደባባዮች የምትቆሙ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ። |
ከዚህ በኋላ አብራም ሎጥን እንዲህ አለው፤ “እኛ ወንድማማች ስለ ሆንን በእኔና በአንተ መካከል እንዲሁም በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ጠብ ሊነሣ አይገባም፤
እግዚአብሔር ሆይ! ልቤ በኩራት የተወጠረ አይደለም፤ ዐይኖቼም ትዕቢተኞች አይደሉም፤ ስለ ታላላቅ ነገሮች ወይም ላስተውለው ስለማልችለው ከባድ ነገር አልጨነቅም።
ተኲላና በግ በአንድነት ይኖራሉ፤ ነብርም ከፍየል ግልገሎች ጋር አብሮ ይመሰጋል፤ ጥጃና የአንበሳ ደቦል አብረው ይመገባሉ፤ ትንሽ ልጅም እየመራ ይጠብቃቸዋል።
በእግዚአብሔር ቅዱስ ተራራ ላይ ምንም ጒዳት አይደርስም፤ ባሕር በውሃ እንደሚሞላ ምድርም እግዚአብሔርን በሚያውቁና በሚያከብሩ ሰዎች ትሞላለች።
እኔም የምለምነው ሁሉም አንድ እንዲሆኑ ነው፤ እንዲሁም አባት ሆይ! አንተ በእኔ እንዳለህ፥ እኔም በአንተ እንዳለሁ፥ እነርሱም በእኛ እንዲኖሩ ነው፤ አንተ እንደ ላክኸኝም ዓለም እንዲያምን ነው።
ወንድሞቼ ሆይ! “መለያየት በመካከላችሁ አይኑር፤ ሁላችሁም ተስማምታችሁ በአንድ ሐሳብና በአንድ ዓላማ ጸንታችሁ ኑሩ” ብዬ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።
በቀረውስ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ በመስማማት ኑሩ፤ የሌላውን ሰው ችግር እንደ ራሳችሁ አድርጋችሁ ቊጠሩ፤ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ ደጎችና ትሑቶች ሁኑ።