መዝሙር 129:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከወጣትነቴ ጀምሮ ጠላቶቼ በጭካኔ አሳደዱኝ፤ ነገር ግን አላሸነፉኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርግጥ ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤ ዳሩ ግን ድል አላደረጉኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከትንሽነቴ ጀምሮ አብዝተው አጠቁኝ፥ ነገር ግን አላሸነፉኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ቃሌን ስማኝ፤ ጆሮህም የልመናዬን ቃል የሚያደምጥ ይሁን። |
ከዚህ በኋላ በብርቱ ሥራ ይጨቊኑአቸው ዘንድ ጨካኞች የሆኑ አሠሪዎችን ሾሙባቸው፤ በዚህም ሁኔታ ዕቃ ማከማቻ የሆኑትን ፊቶምና ራምሴ የተባሉትን ከተሞች ለፈርዖን ሠሩ።
እኔም እንዲህ እልሃለሁ፤ አንተ (ጴጥሮስ)፥ አለት ነህ፤ በዚህችም የመሠረት ድንጋይ ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ ይህችንም ቤተ ክርስቲያን የሞት ኀይል እንኳ አያሸንፋትም።
ይህን ለእናንተ መናገሬ በእኔ ሆናችሁ ሰላም እንዲኖራችሁ ብዬ ነው፤ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፥ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”