ሌዋውያኑም በሕጉ መሠረት ራሳቸውን አንጽተው የሰንበት ቀን በቅድስና የተጠበቀች መሆንዋን ለማረጋገጥ የቅጽር በሮቹን እንዲቈጣጠሩ አዘዝኳቸው። እግዚአብሔር ሆይ! ስለዚህም ሁሉ እንድታስበኝና ስለ ጽኑ ፍቅርህም እንድትታደገኝ እለምንሃለሁ።
መዝሙር 112:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእውነት እርሱ ምንጊዜም ቢሆን አይናወጥም፤ ጻድቅ ሰው ለዘለዓለም ይታሰባል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለዘላለም ከስፍራው አይናወጥምና፤ ጻድቅ ሰው ሲታወስ ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለዘለዓለም አይናወጥም፥ የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰማይና በምድር የተዋረዱትን የሚያይ፤ |
ሌዋውያኑም በሕጉ መሠረት ራሳቸውን አንጽተው የሰንበት ቀን በቅድስና የተጠበቀች መሆንዋን ለማረጋገጥ የቅጽር በሮቹን እንዲቈጣጠሩ አዘዝኳቸው። እግዚአብሔር ሆይ! ስለዚህም ሁሉ እንድታስበኝና ስለ ጽኑ ፍቅርህም እንድትታደገኝ እለምንሃለሁ።
መሥዋዕት የሚቃጠልበትን ማገዶ በተወሰነው ክፍለ ጊዜ ሁሉ ማቅረብ የሚቻልበትን ሁኔታ አደራጀሁ፤ ሰዎቹም ከሚሰበስቡት ሰብል ሁሉ ከእህሉም ሆነ ከፍራፍሬው በመጀመሪያ የደረሰውን እንዴት ማቅረብ እንደሚገባቸው አዘጋጀሁ። አምላኬ ሆይ! ይህን ሁሉ አስብ፤ ይህን በማድረጌም ቸርነት አድርግልኝ።
ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ ንጹሕ ሰዎችን ለመጒዳት ጉቦ የማይቀበል፥ እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ከቶ አይናወጥም። በሰላም ይኖራል እንጂ ከቶ አይናወጥም።
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።