መዝሙር 111:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚያደርገው ሁሉ እውነትና ትክክል ነው፤ ትእዛዞቹም የታመኑ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእጁ ሥራ እውነተኛና ቅን ነው፤ ሥርዐቱም ሁሉ የታመነ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእጆቹ ሥራ እውነትና ፍርድ ናቸው፥ ትእዛዛቱም በሙሉ የታመኑ ናቸው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከክፉ ነገርም አይፈራም፤ በእግዚአብሔር ለመታመን ልቡ የጸና ነው። |
የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ለነፍስ አዲስ ሕይወትን ይሰጣል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ የታመነ ነው፤ ማስተዋል ለጐደላቸው ጥበብን ይሰጣል።
ንጉሡ ናቡከደነፆር እንዲህ አለ፦ “ሰባቱ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ቀና ብዬ ወደ ሰማይ ተመለከትኩ፤ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፤ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገንኩ፤ ለዘለዓለማዊው አምላክ ክብርና ውዳሴ አቀረብኩ፤ “ግዛቱ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፤
“እርሱ ምሽጋችን ነው፤ ሥራዎቹም ፍጹሞች ናቸው፤ መንገዶቹም ሁሉ የቀኑ ናቸው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፥ እርሱም ቀጥተኛና እውነተኛ ነው።