በሌሎች መንደሮችና ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤል ልጆች ካህናቱና ሌዋውያኑ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች በየመንደሮቻቸው ባላቸው ይዞታ ኖሩ። በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የይሁዳ ምድር መሪዎችም ስም ዝርዝር የሚከተለው ነበር፦
መዝሙር 107:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ሊኖሩ ወደሚችሉበት ከተማ በትክክለኛ መንገድ መራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደሚኖሩባትም ከተማ፣ በቀና መንገድ መራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደሚኖሩበት ከተማ ይሄዱ ዘንድ በቀና መንገድን መራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በመቅደሱ ተናገረ፥ ደስ ይለኛል፥ ሰቂማንም እካፈላለሁ፥ የሸለቆ ቦታዎችን እሰፍራለሁ። |
በሌሎች መንደሮችና ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤል ልጆች ካህናቱና ሌዋውያኑ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች በየመንደሮቻቸው ባላቸው ይዞታ ኖሩ። በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የይሁዳ ምድር መሪዎችም ስም ዝርዝር የሚከተለው ነበር፦
ከመንገድ ወጥታችሁ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ብትባዝኑ ከበስተኋላችሁ “ትክክለኛው መንገድ ይህ ነው! በዚህ ሂድ” የሚለውን ድምፅ ትሰማላችሁ።
እናንተን የሚያድን የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፤ “የሚጠቅምህን ሁሉ የማስተምርህና ልትሄድበት የሚገባህን መንገድ የምመራህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ።
እኔ ወደ አገራቸው ስመራቸው ሕዝቤ ከደስታ የተነሣ እያለቀሱና እየጸለዩ ይመለሳሉ። በማይሰናከሉበት የተስተካከለ መንገድ ወደ ጥሩ ውሃ ምንጭ እመራቸዋለሁ። እኔ ለእስራኤል አባት ነኝ፤ ኤፍሬምም የበኲር ልጄ ነው።”
እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “በየጐዳናው ቆማችሁ ተመልከቱ፤ ጥንታዊና መልካም የሆነችው መንገድ የትኛዋ እንደ ሆነች ጠይቃችሁ ተረዱ፤ ባገኛችኋትም ጊዜ በእርስዋ ሂዱ፤ በሰላምም ትኖራላችሁ።” ሕዝቡ ግን “በእርስዋ አንሄድም!” አሉ።
ሁለት ቀንም ይሁን አንድ ወር፥ አንድ ዓመትም ይሁን ከዚያ የረዘመ ጊዜ ደመናው በድንኳኑ ላይ እስካረፈበት ጊዜ ድረስ አይንቀሳቀሱም ነበር፤ ደመናው ሲነሣ ግን ጒዞአቸውን ይቀጥሉ ነበር።
አሁን ግን የሚበልጠውን፥ በሰማይ ያለውን አገር ይናፍቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ከተማን ስላዘጋጀላቸው “አምላካችን” ብለው ቢጠሩት አያሳፍረውም።
እናንተ ግን ወደ ጽዮን ተራራ ቀርባችኋል፤ እርስዋ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ የሆነችው ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ናት፤ በደስታ ወደተሰበሰቡት፥ በብዙ ሺህ ወደሚቈጠሩት መላእክት ቀርባችኋል።
እነርሱ የቀናውን መንገድ ትተው ጠፍተዋል፤ ክፉ በመሥራት የሚገኘውን ገንዘብ የወደደውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከትለው ተሳስተዋል።
የጽድቅን መንገድ ካወቁ በኋላ ከተሰጣቸው ቅዱስ ትእዛዝ ወደ ኋላ ከሚመለሱ ይልቅ የጽድቅን መንገድ ሳያውቁ ቀርተው ቢሆን ኖሮ በተሻላቸው ነበር።