ከዚህ በኋላ ያዕቆብ የምስሩን ወጥ በእንጀራ አድርጎ ሰጠው፤ ዔሳውም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ፤ በዚህ ዐይነት ዔሳው ብኲርናውን በመናቅ አቃለላት።
መዝሙር 106:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስላልተማመኑ መልካሚቷን ምድር ናቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በኋላ መልካሚቱን ምድር ናቁ፤ የተስፋ ቃሉንም አላመኑም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምትወደደውን ምድር ናቁ፥ በቃሉም አልታመኑም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ የእግዚአብሔርን ሥራ፥ በጥልቅም ያለችውን ድንቁን ዐወቁ። |
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ የምስሩን ወጥ በእንጀራ አድርጎ ሰጠው፤ ዔሳውም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ፤ በዚህ ዐይነት ዔሳው ብኲርናውን በመናቅ አቃለላት።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ሆይ! አንቺን እንደ ልጅ አድርጌ በመቀበል፥ ከዓለም እጅግ የተዋበችውንና ለም የሆነችውን ምድር ልሰጥሽ ፈለግኹ፤ ‘አባት’ ብለሽ እንድትጠሪኝና ዳግመኛ ከእኔ እንዳትርቂ በመጠበቅ ነበር።
ከግብጽ ምድር አወጣኋቸው፤ ለእነርሱ የመረጥኩላቸው ምድር በማርና በወተት የበለጸገች ነበረች፤ እርስዋም ከዓለም ምድር ሁሉ ይበልጥ የተዋበች ነበረች፤ ወደዚያች ምድርም እንደማስገባቸው ቃል የገባሁላቸው በዚያን ጊዜ ነው።
ሊሰልሉ ስለ ሄዱበት አገርም ለእስራኤላውያን ያቀረቡት ዘገባ ተስፋ አስቈራጭ ነበር፥ እነርሱም፥ “ልንሰልል የሄድንበት አገር ወደ እርስዋ ለመኖር የሚመጣውን ሰው የምትውጥ ናት፤ እዚያ ያየናቸው ሰዎች ረጃጅሞች ናቸው።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ እኔን የሚንቀው እስከ መቼ ነው? ብዙ ተአምራትን በፊቱ አድርጌአለሁ፤ ታዲያ፥ በእኔ መታመንን እምቢ የሚለው እስከ መቼ ነው?
ስለዚህ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እዚያም የሚኖሩትን ሕዝቦች አትፍሩአቸው፤ እኛ በቀላሉ በጦርነት ድል እንነሣቸዋለን፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፎአል፤ ስለዚህ ፈጽሞ አትፍሩአቸው።”
ይህም ሆኖ የምትሰፍሩበትን ቦታ ለመፈለግና የምትሄዱበትን መንገድ ለማሳየት ቀን በደመና ሌሊት በእሳት፥ በፊታችሁ በሚሄደው በአምላካችሁ በእግዚአብሔር አልተማመናችሁም።
እግዚአብሔር፥ ‘ሂዱ፤ የሰጠኋችሁንም የተስፋ ምድር ውረሱ’ ብሎ ከቃዴስ በርኔ በላካችሁም ጊዜ በእርሱ ላይ ዐመፃችሁ እንጂ አልተማመናችሁበትም፤ ለቃሉም አልታዘዛችሁም።
እንግዲህ ሰማያትን ዘልቆ ወደ ላይ ወደ ሰማይ የወጣ ታላቅ የካህናት አለቃ ስላለን እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ፤ የካህናት አለቃውም የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው።
እነዚያ መልካሙን ዜና በመጀመሪያ የሰሙት ባለመታዘዛቸው እግዚአብሔር ወደሚሰጣቸው የዕረፍት ቦታ አልገቡም፤ ሆኖም ወደዚያ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው አንዳንዶች ነበሩ።
ይህን ሁሉ አስቀድማችሁ አንድ ጊዜ የምታውቁት ቢሆንም እንኳ ጌታ ሕዝቡን ከግብጽ አገር አውጥቶ እንዳዳነና ያላመኑትንም በኋላ እንዳጠፋቸው ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።