Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 106:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ከዚያም በኋላ መልካሚቱን ምድር ናቁ፤ የተስፋ ቃሉንም አላመኑም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የምትወደደውን ምድር ናቁ፥ በቃሉም አልታመኑም፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስላልተማመኑ መልካሚቷን ምድር ናቁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እነ​ርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ፥ በጥ​ል​ቅም ያለ​ች​ውን ድን​ቁን ዐወቁ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 106:24
21 Referencias Cruzadas  

ያዕቆብም ለዔሳው እንጀራና የምስር ወጥ ሰጠው፤ እርሱም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ። ዔሳው ብኵርናውን እንዲህ አድርጎ አቃለላት።


“እኔም፣ “ ‘የተመረጠችውን ምድር፣ የትኛውም ሕዝብ ያላገኘውን የተዋበች ርስት ልሰጥሽ፣ እንደ ወንዶች ልጆቼ ምንኛ በደስታ ልቍጠርሽ’ አልሁ፤ ‘አባቴ’ ብለሽ የምትጠሪኝ፣ እኔንም ከመከተል ዘወር የማትዪ መስሎኝ ነበር።


በዚያ ቀን፣ ከግብጽ አውጥቻቸው ከምድር ሁሉ ይልቅ ውብ ወደሆነችው፣ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው፣ ወዳዘጋጀሁላቸውም ምድር እንደማስገባቸው ማልሁላቸው።


እነዚህም ስለ ሰለሏት ምድር በእስራኤላውያን መካከል እንዲህ የሚል መጥፎ ወሬ አሠራጩ፤ “ያየናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ናት፤ እዚያ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ግዙፎች ናቸው፤


እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ይህ ሕዝብ እስከ መቼ ይንቀኛል? እነዚህን ሁሉ ታምራት በመካከሉ እያደረግሁ የማያምንብኝስ እስከ መቼ ነው?


እስራኤላውያን በሙሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ፤ ማኅበሩም ሁሉ እንዲህ አሏቸው፤ “ምነው በግብጽ ወይም በዚህ ምድረ በዳ ሞተን ባረፍነው ኖሮ!


ይማረካሉ ያላችኋቸውን ልጆቻችሁን ግን አገባቸዋለሁ፤ እናንተ የናቃችኋትን ምድር እነርሱ ይደሰቱባታል።


ብቻ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ እንጐርሳቸዋለንና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሯቸው። ጥላቸው ተገፍፏል፤ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋራ ነውና አትፍሯቸው።”


“ተጋባዦቹ ግን ጥሪውን ችላ ብለው፣ አንዱ ወደ ዕርሻው ሌላው ወደ ንግዱ ሄደ፤


እናንተ ግን ለመውጣት ፈቃደኞች አልነበራችሁም፤ በአምላካችን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐመፃችሁ።


ይህም ሆኖ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር አልታመናችሁም፤


እግዚአብሔር ከቃዴስ በርኔ ባስወጣችሁ ጊዜ፣ “ውጡ፤ የሰጠኋችሁንም ምድር ርስት አድርጋችሁ ውረሷት” አላችሁ። እናንተ ግን በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐመፃችሁ፤ እርሱን አልታመናችሁበትም፤ አልታዘዛችሁትምም።


ለአንድ ጊዜ መብል ሲል ብኵርናውን እንደ ሸጠው እንደ ዔሳው፣ ማንም ሴሰኛ ወይም እግዚአብሔርን የማያከብር ሆኖ እንዳይገኝ ተጠንቀቁ።


ወንድሞች ሆይ፤ ከእናንተ ማንም ከሕያው እግዚአብሔር የሚያስኰበልል፣ ኀጢአተኛና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ።


እንግዲህ ወደ ሰማያት ያረገ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፣ እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ።


ለእነዚያ እንደ ተሰበከ ለእኛም ደግሞ ወንጌል ተሰብኮልናልና። ነገር ግን ሰሚዎቹ ቃሉን ከእምነት ጋራ ስላላዋሐዱት አልጠቀማቸውም።


ወደ ዕረፍቱ ገና የሚገቡ አንዳንዶች አሉ፤ ቀድሞ የምሥራቹ ቃል የተሰበከላቸው ባለመታዘዛቸው ምክንያት ወደ ዕረፍት አልገቡም።


ምንም እንኳ አስቀድማችሁ ይህን ሁሉ የምታውቁ ቢሆንም፣ ጌታ ሕዝቡን ከግብጽ ምድር እንዴት እንዳወጣ፣ በኋላ ግን ያላመኑትን እንዳጠፋ ላስታውሳችሁ እወድዳለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos