ዕቅዱን ለሙሴ ገለጠለት፤ የእስራኤል ሕዝቦች አስደናቂ ሥራዎቹን እንዲያዩ አደረገ።
መንገዱን ለሙሴ፣ ሥራውንም ለእስራኤል ሕዝብ አሳወቀ።
ለሙሴ መንገዱን አስታወቀ፥ ለእስራኤል ልጆችም ድንቅ ሥራዎቹን።
ከተግሣጽህም የተነሣ ይሸሻሉ፥ ከነጐድጓድህም ድምፅ የተነሣ ይደነግጣሉ፤
የተቀደሰውን ሰንበትህንም እንዲያውቁ አደረግሃቸው፤ በአገልጋይህም በሙሴ አማካይነት ትእዛዞችህን፥ ድንጋጌህንና ሕጎችህን ሰጠሃቸው።
በዚያ ሳሉ ያደረገላቸውን አስደናቂ ነገሮችና፥ በቀይ ባሕርም ያደረገላቸውን አስገራሚ ነገሮች ዘነጉ።
የሕዝቦችን ርስት በመስጠት ታላቅ ኀይሉን ለወገኖቹ አሳይቶአል።
ቃሉን ለያዕቆብ ልጆች ሕጉንና ሥርዓቱንም ለእስራኤል ይሰጣል።
እረኛ የበጎችን መንጋ እንደሚመራ፥ አንተም በሙሴና በአሮን አማካይነት ሕዝብህን መራህ።
ያሳያቸውን ተአምራት ሁሉ እና ያደረገውን መልካም ነገር ሁሉ ረሱ።
እርሱ ሥርዓትን ለያዕቆብ ልጆች ዐወጀ፤ ለእስራኤልም ሕግን መሠረተ፤ ልጆቻቸውንም እንዲያስተምሩ የቀድሞ አባቶቻችንን አዘዛቸው።
በደመና ዐምድ ሆኖ ተናገራቸው፤ የሰጣቸውንም ደንብና ድንጋጌ ፈጸሙ።
እግዚአብሔር በሲና ተራራ ራስ ላይ ወርዶ፥ ወደ ተራራው ጫፍ እንዲመጣ ሙሴን ጠራው፤ ሙሴም ወደ ተራራው ጫፍ ወጣ፤
ከዚህም በኋላ ሁሉም በአንድ ድምፅ ተባብረው “እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ እንፈጽማለን” አሉ፤ ሙሴም ይህንኑ ለእግዚአብሔር አቀረበ።
ሕዝቡ ግን ርቀው ቆሙ፤ ሙሴ ብቻውን እግዚአብሔር ወዳለበት ጥቅጥቅ ወደ ሆነው ደመና ተጠጋ።
አሁንም በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ ዐውቅ ዘንድ እንዳገለግልህና አንተን በማስደሰት እንድቀጥል እባክህ መንገድህን አሳየኝ፤ ይህም ሕዝብ ሕዝብህ እንደ ሆነ ተመልከት።”
ከአገልጋዬ ከሙሴ ጋር የምነጋገረው ግን እንደዚያ አይደለም፤ እርሱ በቤቴ ሁሉ የታመነ ነው፤
እግዚአብሔር ፊት ለፊት ያነጋገረው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ በእስራኤል ከቶ ተነሥቶ አያውቅም፤