መዝሙር 103:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባት ለልጆቹ የሚራራላቸውን ያኽል እግዚአብሔርም የሚፈሩትን ይራራላቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፣ እግዚአብሔር ለሚፈሩት እንዲሁ ይራራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ ጌታም ለሚፈሩት ይራራል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተራሮችን ከውስጣቸው የሚያጠጣቸው፤ ከሥራህ ፍሬ ምድር ትጠግባለች። |
“እስራኤል ሆይ! እናንተ የተወደዳችሁ ልጆቼ ናችሁ፤ ከሁሉ አስበልጬ የምወዳችሁ አይደለምን? ምሕረት አደርግላችሁ ዘንድ ወደ እኔ ላቀርባችሁ እፈቅዳለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
እኔ ወደ አገራቸው ስመራቸው ሕዝቤ ከደስታ የተነሣ እያለቀሱና እየጸለዩ ይመለሳሉ። በማይሰናከሉበት የተስተካከለ መንገድ ወደ ጥሩ ውሃ ምንጭ እመራቸዋለሁ። እኔ ለእስራኤል አባት ነኝ፤ ኤፍሬምም የበኲር ልጄ ነው።”
ይሁን እንጂ በጠላቶቻቸው አገር ሳሉ እንኳ እስከ መጨረሻ አልተዋቸውም ወይም አልደመስሳቸውም፤ ይህማ ቢሆን ኖሮ ከእነርሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን እስከ መጨረሻ ባልጠበቅሁም ነበር፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝ።
ጡት የሚጠባውን ሕፃን አንዲት ሞግዚት እንደምትታቀፈው እኔም እነርሱን ታቅፌ አንተ ለአባቶቻቸው በመሐላ ቃል ወደ ገባህላቸው ምድር እንዳደርሳቸው የምታደርገኝ እነዚህን ሰዎች እኔ ፀነስኳቸውን? ወይስ እኔ ወለድኳቸውን?
ኢየሱስ “ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሂጂና ‘እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፥ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ ብሎአል’ ብለሽ ንገሪያቸው” አላት።
እነዚህም ሁሉ ከተሞች ከፍ ያለ ቁመት ባላቸው ቅጽሮች የተመሸጉ ነበሩ፤ የቅጽሮቹም በሮች በመወርወሪያ የሚዘጉ ነበሩ፤ ቅጽር የሌላቸው ብዙ መንደሮችም ነበሩ።