መዝሙር 10:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰው በሁሉ ነገር ይሳካለታል፤ የእግዚአብሔርን ፍርድ ግን ሊረዳ አይችልም፤ በጠላቶቹም ላይ ይሳለቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንገዱ ዘወትር የተሳካ ነው፤ ዕቡይ፣ ከሕግህም የራቀ ነው። በመሆኑም በጠላቶቹ ላይ ያፌዛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንገዱ ሁልጊዜ የጸና ነው፥ ፍርድህ ከእርሱ በላይ እጅግ ከፍ ያለ ነው፥ በጠላቶቹ ላይ ግን ይቀልዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ጻድቁንና ኃጥኡን ይመረምራል፤ ዐመፃን የወደዳት ግን ነፍሱን ጠልቶአል። |
ንጉሡና ሰዎቹ ከኢያቡሳውያን ጋር ለመዋጋት በኢየሩሳሌም ላይ ዘመቱ፤ ዳዊት ወደዚያ የማይገባ መስሎአቸው የምድሪቱ ነዋሪዎች ዳዊትን “አንተ ወደዚህ ልትገባ አትችልም፤ ዕውሮችና አንካሶች እንኳ ይመልሱሃል” አሉት።
በዚህን ጊዜ አንድ ነቢይ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “እግዚአብሔር ‘ከቤንሀዳድ ሠራዊት ብዛት የተነሣ አትፍራ! እኔ ዛሬ በዚህ ሠራዊት ላይ ድልን እንድትቀዳጅ አደርጋለሁ፤ አንተም ደግሞ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃለህ’ ይልሃል” አለው።
እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።
በሕገ ወጥ መንገድ ሀብትን የሚሰበስቡ ሰዎች ያ የሰበሰቡት ሀብት ሕይወታቸውን ያጠፋዋል። በግፍም የሚበለጽጉ ሰዎች ዕድል ፈንታቸው ይኸው ነው።
አምላክ ሆይ፥ ክንድህ ለመቅጣት ተነሥቶአል፤ አንተን የሚጠሉ ሰዎች አያዩትም፤ ለሕዝብህ ምን ያኽል ቅናት እንዳለህ አይተው ይፈሩ፤ ለጠላቶችህ ባዘጋጀኸው ቅጣት ይጥፉ።
“ከሞት ጋር ስምምነት አድርገናል፤ ከሙታንም ዓለም ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል” እያላችሁ ትመካላችሁ፤ እንዲሁም “ማታለልን እንደ መጠለያ፥ ሐሰትንም እንደ መጠጊያ አምባ ስላደረግን መቅሠፍት በሚመጣበት ጊዜ ሳይነካን ያልፋል” ብላችሁ ተስፋ ታደርጋላችሁ።
ስለዚህ የቊጣውን ግለትና አስፈሪውን ጦርነት በላያችን ላይ አወረደ፤ በዙሪያችን እሳት አቀጣጠለ፤ እኛ ግን ይህን ሁሉ አልተረዳነውም፤ አቃጠለን ልብም አላደረግነውም።
ጥበብ ያላቸው እነዚህን ነገሮች ይረዳሉ፤ አስተዋዮችም ያውቋቸዋል፤ የእግዚአብሔር መንገድ ትክክል ነው፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ኃጢአተኞች ግን ይሰናከሉበታል።
ሁሉም ወደ ወይን ተክሎቻቸው ወጥተው የወይን ፍሬ ለቀሙ፤ የወይን ጠጅ ጠምቀው ትልቅ በዓል አደረጉ፤ ወደ አምላካቸውም መቅደስ ገብተው በዚያ እየበሉና እየጠጡ ስለ አቤሜሌክ በማፌዝ ተናገሩ።
ከዚህ በኋላ ዘቡል እንዲህ አለው፤ “ያ ሁሉ ፉከራህ አሁን የት ደረሰ? ‘አቤሜሌክ የተባለውን ሰው የምናገለግለው ለምንድን ነው?’ ብለህ የጠየቅህ አንተ አልነበርክምን? በማፌዝ ስታላግጥባቸው የነበርከው ሰዎች እነሆ፥ እነዚህ ናቸው፤ በል ወጥተህ ጦርነት ግጠማቸው፤”