Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 73:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ይህም የሆነው ትዕቢተኞችና ክፉዎች ሰዎች ሲበለጽጉ በማየቴ ቅናት አድሮብኝ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ክፉዎች ሲሳካላቸው አይቼ፣ በዐመፀኞች ቀንቼ ነበርና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የክፉዎችን ሰላም አይቼ በዓመፀኞች ቀንቼ ነበርና።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ጠላት በቅ​ዱ​ሳ​ንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁል​ጊዜ በት​ዕ​ቢ​ታ​ቸው ላይ እጅ​ህን አንሣ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 73:3
14 Referencias Cruzadas  

“ክፉ ሰዎች ዕድሜአቸው ረዝሞ፥ ሃብታቸው በዝቶ በምድር ላይ ስለምን ይኖራሉ?


እግዚአብሔር ሆይ! ከአንተ ጋር በምከራከርበት ጊዜ ሁሉ አንተ ትክክለኛ ነህ፤ አሁን ግን ስለ ትክክለኛ ፍርድ ጥያቄ አለኝ፤ የኃጢአተኛ ሕይወት የተቃና የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? አታላዮችስ ሁሉ ነገር የሚሳካላቸው ስለምንድን ነው?


በኃጢአተኞች ላይ አትቅና፤ እግዚአብሔርን መፍራት የዘወትር ሐሳብህ ይሁን፤


በትዕግሥት ጸንተህ እግዚአብሔር የሚያደርገውን ለማየት ተጠባበቅ፤ ሌሎች ሰዎች ክፉ ሐሳባቸው ቢሳካላቸው አትበሳጭ።


በክፉዎች ምክንያት አትበሳጭ፤ ኃጢአት በሚሠሩም አትቅና።


በክፉ ሰዎች አትቅና፤ ከእነርሱም ጋር ጓደኛ ለመሆን አትፈልግ፤


ደግሞስ ቅዱስ መጽሐፍ “እግዚአብሔር በውስጣችሁ ያሳደረው መንፈስ ለእርሱ ብቻ እንድንሆን በብርቱ ይመኛል” ያለው በከንቱ ነውን?


በግፈኞች ሰዎች አትቅና፤ ክፉ ሥራቸውንም አትከተል።


ኀይላቸውን እንደ አምላክ አድርገው የሚቈጥሩ ሌቦችና እግዚአብሔርን የካዱ ሰዎች እንኳ በሰላም ይኖራሉ።


እውነተኞች በዚህ ነገር ተደናግጠዋል፤ ንጹሖች እግዚአብሔርን በማያምኑ ሰዎች ላይ ተቈጥተዋል።


እግዚአብሔር በሰላም እንዲኖሩ ቢፈቅድላቸውም እንኳ የሚሄዱበትን መንገድ ሁሉ አተኲሮ ይመለከታል።


ክፉ ሰው በሁሉ ነገር ይሳካለታል፤ የእግዚአብሔርን ፍርድ ግን ሊረዳ አይችልም፤ በጠላቶቹም ላይ ይሳለቃል።


ከንቱ በሆነው ዘመኔ ክፉ ሰው በሚሠራው በደል እስከ ረጅም ዕድሜ ሲኖር፥ ደግ ሰው ግን በደግነቱ ሲጠፋ ብዙ ነገር አይቼበታለሁ፤


እንደምናየው ከሆነ እነሆ፥ ክፉ አድራጊዎች ዕድለኞች ናቸው፤ በእርግጥም እነርሱ በብልጽግና ይኖራሉ፤ እግዚአብሔርን እንኳ እየተፈታተኑት ምንም ችግር አይደርስባቸውም እያላችሁ ትናገራላችሁ።’ ”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios