ምሳሌ 8:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እውነት የሆነውን እናገራለሁ፤ ክፋት በእኔ ዘንድ የተጠላ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንደበቴ እውነትን ይናገራል፤ ከንፈሮቼ ክፋትን ይጸየፋሉና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አፌ እውነትን ይናገራልና፥ ከንፈሮቼም ክፋትን ይጸየፋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንደበቴ እውነትን ታስተምራለችና፥ የሐሰት ከንፈሮችም በፊቴ የረከሱ ናቸውና። |
ጲላጦስም “ታዲያ፥ አንተ ንጉሥ ነኻ?” አለው። ኢየሱስም “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንኩ አንተ ትላለህ፤ እኔ የተወለድኩትና ወደ ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ልመሰክር ነው፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰማል” ሲል መለሰ።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ምንም እንኳ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ከየት እንደ መጣሁ፥ ወዴትም እንደምሄድ ስለማውቅ ምስክርነቴ እውነት ነው፤ እናንተ ግን ከየት እንደ መጣሁና ወዴት እንደምሄድ አታውቁም።
ይህንንም ስናገር እግዚአብሔር ለቀደሙት አባቶች የሰጠው ተስፋ እንዲፈጸምና የእግዚአብሔርም እውነተኛነት እንዲታወቅ ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ ሆነ ማለቴ ነው።
“ለሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ “ይህ፥ አሜን ከሆነው፥ ታማኝና እውነተኛ ምስክር ከሆነው፥ የእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ መገኛ ከሆነው የተነገረ ነው፤