ምሳሌ 7:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕውቀት ከጐደላቸው ሰዎች መካከል ወጣቶችን ተመለከትኩ፤ ከእነርሱም መካከል አስተሳሰብ የጐደለው አንድ ወጣት አየሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልበ ቢሱን ወጣት፣ ከአላዋቂዎች መካከል አየሁት፤ ከጕልማሶችም መካከል ለየሁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአላዋቂዎች መካከል አስተዋልሁ፥ ከወጣቶችም መካከል አንዱ አእምሮ ጐድሎት አየሁ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአላዋቂዎች ወጣቶች መካከል ከዕውቅት ድሃ የሆነውን ጐልማሳ ብታይ፥ |
የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ለነፍስ አዲስ ሕይወትን ይሰጣል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ የታመነ ነው፤ ማስተዋል ለጐደላቸው ጥበብን ይሰጣል።
“እናንተ ዕውቀት የጐደላችሁ! እስከ መቼ ድረስ የሞኝነትን መንገድ ትከተላላችሁ! እናንተስ ፌዘኞች! እስከ መቼ ድረስ በማፌዝ ትደሰታላችሁ! ሞኞችስ እስከ መቼ ድረስ ዕውቀትን ትጠላላችሁ!
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እኔን የማያውቁ ሞኞች ሆነዋል፤ ማስተዋል ስለ ጐደላቸው እንደ ሕፃናት የሚታለሉ ናቸው፤ ክፉ ነገር ለመሥራት የተራቀቁ ብልኆች ናቸው፤ መልካም ነገር ማድረግ ግን ከቶ አይሆንላቸውም።”