አንድ ቀን ኤልሳዕ አንዲት ሀብታም ሴት ወደምትኖርበት ወደ ሱነም ሄደ፤ እርስዋም ምግብ እንዲበላ ጋበዘችው፤ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ወደ ሱነም በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ በቤትዋ ይመገብ ነበር፤
ምሳሌ 7:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሚማርኩ ቃሎችዋ አግባባችው፤ በለዘበ አነጋገርዋም አታለለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሚያግባቡ ቃላት አሳተችው፤ በለሰለሰ አንደበቷ አታለለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በብዙ ጨዋታዋ እንዲስት ታደርገዋለች፥ በከንፈርዋ ልዝብነት ትጐትተዋለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በብዙ ጨዋታዋ እንዲስት ታደርገዋለች፤ በከንፈርዋ ወጥመድም ትጐትተዋለች። |
አንድ ቀን ኤልሳዕ አንዲት ሀብታም ሴት ወደምትኖርበት ወደ ሱነም ሄደ፤ እርስዋም ምግብ እንዲበላ ጋበዘችው፤ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ወደ ሱነም በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ በቤትዋ ይመገብ ነበር፤
ስለዚህ የቤቱ ጌታ አገልጋዩን እንዲህ አለው፦ ‘ቤቴ እንዲሞላ ወደ ገጠር በሚወስዱት ጐዳናዎችና ስላች መንገዶች ሂደህ ሌሎች እንዲመጡ አድርግ!
እነርሱ ግን “ቀኑ መሽቶአል፤ ፀሐይም መጥለቅዋ ነው፤ ስለዚህ ከእኛ ጋር እዚህ ዕደር” ብለው አጥብቀው ለመኑት፤ በዚህ ምክንያት ከእነርሱ ጋር ሊያድር ወደ ቤት ገባ።
እርስዋና በቤትዋ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ፥ “በጌታ የማምን መሆኔን ካረጋገጣችሁልኝ ወደ ቤቴ መጥታችሁ ተቀመጡ” ስትል አጥብቃ ለመነችን።
ከዚህም የተነሣ እርስዋ በሠርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ አለቀሰች፤ አጥብቃም ስለ ነዘነዘችው የእንቆቅልሹን ፍች በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርስዋም ሄዳ ለፍልስጥኤማውያኑ ነገረቻቸው።
ሳኦል “ምንም ነገር አልቀምስም” ብሎ እምቢ አለ፤ ይሁን እንጂ ባለሟሎቹም እንዲመገብ አበረታቱት፤ በመጨረሻም “እሺ” ብሎ ከወደቀበት መሬት በመነሣት አልጋ ላይ ተቀመጠ፤