ምሳሌ 7:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያንን ወጣት ዕቅፍ አድርጋ ሳመችው፤ ያለ ኀፍረት እንዲህ አለችው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አፈፍ አድርጋ ይዛ ሳመችው፤ ኀፍረቷንም ጥላ እንዲህ አለችው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዘችውም ሳመችውም፥ ፊትዋም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዘችውም ሳመችውም፤ ፊቷም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው፦ |
አመንዝራ ሴት ገንዘብ ይከፈላት ነበር፤ አንቺ ግን ገንዘብ በመቀበል ፈንታ ለወዳጆችሽ ስጦታ ታበረክቺአለሽ፤ ከየአቅጣጫው መጥተው ከአንቺ ጋር ያመነዝሩ ዘንድ መደለያ ገንዘብ ሰጠሽ።
“ነገር ግን የሰው ልጅ ሆይ! እነርሱንም ሆነ የሚናገሩትን ቃል አትፍራ፤ እንደ እሾኽና እንደ አሜከላ ሆነውብህ በጊንጦች መካከል እንደምትኖር ሆነህ ቢሰማህም ቃላቸውንም ሆነ የእነዚያን ዐመፀኞች የቊጣ ፊት ከቶ አትፍራ።
በፔዖር ሳለን የበለዓምን ምክር ተቀብለው ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት እንዲተዉ ያደረጉ ሴቶች መሆናቸውን ዘነጋችሁን? በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ የአባር ቸነፈር መቅሠፍት ያመጣም ያ ስሕተት ነበር።
ነገር ግን አንድ የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ ይኸውም ‘ነቢይት ነኝ’ የምትለዋን ሴት ኤልዛቤልን ችላ ብለህ ታግሠሃታል፤ እርስዋ አገልጋዮቼ እንዲሴስኑና ለጣዖት የተሠዋ ምግብ እንዲበሉ በማስተማር አሳስታቸዋለች።