ምሳሌ 3:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በክፉ ሰዎች ላይ በድንገት የሚደርስ አደጋና ጥፋት ይደርስብኛል ብለህ አትፍራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንገተኛን መከራ፣ በክፉዎች ላይ የሚደርሰውንም ጥፋት አትፍራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንገት ከሚያስፈራ ነገር፥ ከሚመጣውም ከኀጥኣን ጥፋት አትፈራም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሚመጣብህም አስደንጋጭ ነገር፥ ከሚመጣውም የክፉዎች ሰዎች አደጋ አትፈራም፤ |
በፍትሕና በእውነት ላይ ትመሠረቺአለሽ፤ ግፍና ጭቈና ከአንቺ ይርቃል የሚያስፈራሽም የለም፤ ሽብርም ከአንቺ ይርቃል፤ ወደ አንቺም አይቀርብም።
እያንዳንዱ ሰው በተከለው ወይንና በለስ ጥላ ሥር በሰላም ያርፋል። የሚያስፈራውም ነገር አይኖርም፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።
ከዚህ በኋላ ምድሬን ዙሪያዋን ከብቤ እጠብቃለሁ፤ የወራሪ ኀይል መተላለፊያም አላደርጋትም። ሕዝቤ ምን ያኽል እንደ ተሠቃየ ስለ ተመለከትኩ ከእንግዲህ ወዲህ ጨቋኞች አይወሩአቸውም።”