ምሳሌ 3:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምትተኛበት ጊዜ አትፈራም፤ ሌሊቱንም ሙሉ የሰላም እንቅልፍ ታገኛለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስትተኛ አትፈራም፤ ትተኛለህ እንቅልፍህም ጣፋጭ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተኛህ ጊዜ አትፈራም፥ ስትተኛም፥ እንቅልፍህ የጣፈጠ ይሆንልሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተቀመጥህም ጊዜ አትፈራም፤ ብትተኛም መልካም እንቅልፍ ትተኛለህ። |
በማለዳ እየተነሡና በምሽትም እየዘገዩ ለኑሮ መድከም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ሰዎች ገና ተኝተው ሳሉ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ያዘጋጅላቸዋል።
የጉልበት ሥራ የሚሠራ ሰው ብዙም ሆነ ጥቂት ቢመገብ የሰላም እንቅልፍ አግኝቶ ያድራል፤ የባለ ጸጋ ሰው የሀብት ብዛት ግን ሀብቱ እንቅልፍ ይነሣዋል።
በፍትሕና በእውነት ላይ ትመሠረቺአለሽ፤ ግፍና ጭቈና ከአንቺ ይርቃል የሚያስፈራሽም የለም፤ ሽብርም ከአንቺ ይርቃል፤ ወደ አንቺም አይቀርብም።
የሰላም ዋስትና የሚያገኙበትን ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር እገባለሁ፤ አደገኞች የሆኑትን አራዊት ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፤ ስለዚህ በጎቼ በየመስኩ በሰላም ተሰማርተው ሊኖሩና በየጫካውም ሊያድሩ ይችላሉ።
ዛፎች ያፈራሉ፤ እርሻዎች በቂ የእህል ምርት ይሰጣሉ፤ እያንዳንዱም በገዛ ራሱ ምድር በሰላም ይኖራል፤ የሕዝቤን ቀንበር ሰብሬ ባሪያ አድርገው ከሚገዙአቸው ጨቋኞች እጅ ነጻ ሳወጣቸው እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።
“በምድራችሁ ሰላምን እሰጣችኋለሁ፤ ማንንም ሳትፈሩ ያለ ስጋት ትተኛላችሁ፤ አደገኞች የሆኑ አራዊትን ከምድራችሁ አስወግዳለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ጦርነት በዚያ አይኖርም።
ሄሮድስ በማግስቱ ጴጥሮስን ለሕዝቡ ሊያቀርበው አስቦ ነበር፤ ጴጥሮስም በዚያች ሌሊት በሁለት ሰንሰለት ታስሮ በሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር፤ ሌሎች ወታደሮችም የወህኒ ቤቱን በር ይጠብቁ ነበር።