ምሳሌ 29:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰዎች ሥልጣን ሲይዙ ሕግ መተላለፍ ይበዛል፤ ደጋግ ሰዎች ግን የክፉ ሰዎችን ውድቀት ሳያዩ አይሞቱም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ኀጢአት ይበዛል፤ ጻድቃን ግን የእነርሱን ውድቀት ያያሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ ሰዎች ሥልጣን ሲይዙ ሕግ መጣስ ይበዛል፥ ጻድቃን ግን ውደቀታቸውን ያያሉ። |
ጌታ ሆይ! አንተን የማይፈራና ስምህንም የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ፤ የእውነት ፍርድህ ስለ ተገለጠ፥ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።”
ሰማይ ሆይ! በእርስዋ ደስ ይበልህ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ በእርስዋ ላይ ስለ ፈረደባት እናንተ ቅዱሳንና ሐዋርያት ነቢያትም ደስ ይበላችሁ!