ምሳሌ 27:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቊጣ ጭካኔና ንዴትን ያስከትላል፤ ቅናት ግን ከቊጣ የባሰ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንዴት ጨካኝ፣ ቍጣም ጐርፍ ነው፤ በቅናት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁጣ ጭካኔን ያስከትላል፥ ንዴትም እንደ ጎርፍ ነው፥ በቅንዓት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል? |
ኦናን የሚወለዱት ልጆች የእርሱ ያለመሆናቸውን በማወቁ ወደ ወንድሙ ሚስት ሲገባ ዘሩን ወደ ምድር ያፈሰው ነበር፤ በዚህ ዐይነት በወንድሙ ስም ልጆች እንዳይወለዱ አደረገ።
በዘለዓለማዊ ፍቅር በልብህ ውስጥ እንደ ማኅተም አትመኝ፤ በክንድህም እንደ ማኅተም እኔን ብቻ ያዘኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናት፤ ቅናትም እንደ መቃብር የከፋች ናት፤ የእሳትዋ ወላፈን እንደ እግዚአብሔር ወላፈን ነው።
አይሁድ ግን ቀንተው የሚበጠብጡ ሥራ ፈቶችን ከየመንገዱ ሰበሰቡና አሳደሙ። በከተማው ውስጥ ብጥብጥ እንዲነሣ አደረጉ፤ ጳውሎስንና ሲላስን አውጥተው ለሕዝቡ ለመስጠትም የኢያሶንን ቤት ከበቡ።
ስለዚህ በበደል፥ በክፋት፥ በሥሥት፥ በተንኰል፥ በምቀኝነት፥ በነፍሰገዳይነት፥ በጥል፥ በአታላይነት፥ በክፉ ምኞት ሁሉ የተሞሉ፥ እንዲሁም ሐሜተኞች ናቸው፤
የሰይጣን ወገን እንደ ነበረውና ወንድሙን እንደ ገደለው እንደ ቃየል መሆን አይገባንም፤ እርሱ ወንድሙን ስለምን ገደለው? የእርሱ ሥራ ክፉ ስለ ነበረና የወንድሙ ሥራ ግን ትክክል ስለ ነበረ ነው።