Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 14:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ሰላም ያለው አእምሮ ለሰውነት ጤንነትን ያስገኛል፤ ቅንአት ግን አጥንትን ያደቃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ሰላም ያለው ልብ ለሰውነት ሕይወት ይሰጣል፤ ቅናት ግን ዐጥንትን ያነቅዛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ትሑት ልብ የሥጋ ሕይወት ነው፥ ቅንዓት ግን አጥንትን ያነቅዛል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 የሚያስታርቅ ሰው የልብ ፈዋሽ ነው፤ ቀናተኛ ልብ ግን ለአጥንት ነቀዝ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 14:30
14 Referencias Cruzadas  

እርሱም “እኔን ያበሳጨኝ ከናቡቴ ያገኘሁት መልስ ነው፤ ይኸውም የእርሱን የወይን ተክል ቦታ እንድገዛ ወይም ከፈለገ ልዋጩን እንድሰጠው ብጠይቀው የወይን ተክል ቦታውን ‘በምንም ዐይነት አልሰጥህም’ ብሎ አናደደኝ” ሲል መለሰላት።


ቊጣ ሞኝን ይገድለዋል፤ ቅናትም ሰውን ያጠፋል።


ክፉዎች ይህን አይተው ይቈጣሉ፤ ተስፋ በመቊረጥም ጥርሳቸውን ያፋጫሉ፤ የክፉዎችም ምኞት ከንቱ ይሆናል።


ኀፍረት እንዳይደርስብኝ ሕግህን በትክክል እንድፈጽም እርዳኝ።


አስተዋይ ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤ ባልዋን የምታሳፍር ሴት ግን አጥንትን እንደሚያደቅ በሽታ ናት። እንደሚጐዳ ነቀርሳ በሽታ ትሆንበታለች።


የልብ ደስታ ፊትን ያበራል፤ የልብ ሐዘን ግን መንፈስን ያደቃል።


ደስተኛነት ለልብ መልካም መድኃኒት ነው፤ የመንፈስ ሐዘንተኛ መሆን ግን አጥንትን ይሰብራል።


ይህን ብታደርግ ለሰውነትህ ጤንነትን፥ ለአጥንቶችህም ጥንካሬን ታገኛለህ።


ልብ የሕይወት ምንጭ ስለ ሆነ ልብህን ከሁሉ ነገር አስበልጠህ ጠብቀው።


ይህን ሁሉ ስሰማ ሰውነቴ ይርበደበዳል፤ ድምፁም ከንፈሮቼን ያንቀጠቅጣል፤ አጥንቶቼ ይበሰብሳሉ፤ እግሮቼ ከታች ይብረከረካሉ፤ በጠላቶቻችን ላይ መከራ የሚደርስበትን ጊዜ በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።


“የያዕቆብ ልጆች በወንድማቸው በዮሴፍ ላይ ቀንተው በግብጽ አገር ባሪያ እንዲሆን ሸጡት፤ እግዚአብሔር ግን ከእርሱ ጋር ነበረ፤


ስለዚህ በበደል፥ በክፋት፥ በሥሥት፥ በተንኰል፥ በምቀኝነት፥ በነፍሰገዳይነት፥ በጥል፥ በአታላይነት፥ በክፉ ምኞት ሁሉ የተሞሉ፥ እንዲሁም ሐሜተኞች ናቸው፤


እግዚአብሔር የሰጠን የኀይልና የፍቅር፥ ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አይደለም።


ደግሞስ ቅዱስ መጽሐፍ “እግዚአብሔር በውስጣችሁ ያሳደረው መንፈስ ለእርሱ ብቻ እንድንሆን በብርቱ ይመኛል” ያለው በከንቱ ነውን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos