5 በግልጽ የሚነገር ተግሣጽ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል።
5 የተገለጠ ዘለፋ፣ ከተደበቀ ፍቅር ይሻላል።
5 ግልጽ ተግሣጽ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል።
ሰውን ከማቈላመጥ ይልቅ እየመከረ የሚገሥጸውን ሰው በመጨረሻ ያመሰግነዋል።
ሌሎች እንዲፈሩ ኃጢአት የሚሠሩትን በሰዎች ሁሉ ፊት ገሥጽ።
የእነርሱ አድራጎት ከወንጌል እውነት ጋር አለመስማማቱን ባየሁ ጊዜ ጴጥሮስን “አንተ አይሁዳዊ ሆነህ ሳለ በአይሁድ ሥርዓት ሳይሆን በአሕዛብ ሥርዓት ትኖር ነበር። ታዲያ፥ አሕዛብ በአይሁድ ሥርዓት እንዲኖሩ ለምን ታስገድዳቸዋለህ?” ስል በሁሉም ፊት ተቃወምኩት።
“ወንድምህ ቢበድልህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ በደሉን ንገረው፤ ቢሰማህ እንደገና ወንድምህ እንዲሆን ታደርገዋለህ፤
“ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ በእርሱ ምክንያት ኃጢአት እንዳይሆንብህ ገሥጸው።