ምሳሌ 27:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብት ለዘወትር የሚኖር አይደለም፤ መንግሥታትም ቢሆኑ ዘለዓለም አይኖሩም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሀብት ለዘላለም አይኖርምና፤ ዘውድም ከትውልድ ወደ ትውልድ ጸንቶ አይኖርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሃብት ለዘለዓለም አይኖርምና፥ ዘውድም ለትውልድ ሁሉ አይጸናምና። |
በዚህ ዓለም እጅግ የሚያሳዝን ክፉ ነገር ደግሞ አየሁ፤ ይኸውም ሰዎች ለክፉ ቀን ይጠቅመናል ብለው ሀብት ያከማቻሉ፤ ነገር ግን በአንድ መጥፎ አጋጣሚ ሀብታቸውን ያጡና ለልጆቻቸው የሚተላለፍ ምንም ነገር ሳይተርፋቸው ይቀራል።
ለንጉሣዊ ሥልጣኑ ወሰን የለውም፤ መንግሥቱም ዘለዓለማዊ ሰላም የሰፈነበት ይሆናል፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም፥ እውነትና ፍትሕ የሰፈነበት መንግሥት በዳዊት ዙፋን ላይ ተመሥርቶ እንዲጸና ያደርገዋል፤ የሠራዊት አምላክ ቅናት ይህን ለማድረግ ወስኖአል።
እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ የራስ ዘውድህን አንሣ! ጥምጥምህን አውልቅ! ነገሮች እንደ ነበሩ አይቀሩም፤ ዝቅተኞችን በሥልጣን ከፍ አድርገህ አሁን ገዢዎች የሆኑትን ዝቅ አድርጋቸው!
እግዚአብሔር ቊጣውን በሚገልጥበት በዚያን ቀን ሰዎችን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እንደ እሳት ባለው ቅናቱ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ ይህም የሚሆነው በዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በድንገት የሚያልቁ ስለ ሆነ ነው።
አሁን ግን መንግሥትህ ዘላቂ አይሆንም፤ እግዚአብሔር እንደ ልቡ የሚሆንለትን ሰው መርጦአል፤ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዝ ስላልጠበቅህ እርሱን በሕዝቡ ላይ መሪ ይሆን ዘንድ ቀብቶታል።”