ምሳሌ 2:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ለቀጥተኞች መልካም ጥበብን ይሰጣል፤ በተግባራቸው ነቀፋ ለሌለባቸው ጋሻቸው ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ለቅኖች ትክክለኛ ጥበብ ያከማቻል፤ ያለ ነቀፋ ለሚሄዱትም ጋሻ ይሆናቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ለቅኖች ስምረትን ያከማቻል፥ ያለ ነቀፋ ለሚሄዱትም ጋሻ ነው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ቅንነትን ለሚያደርጉ ደኅንነትን ያከማቻል፤ በመንገዳቸውም ይቆምላቸዋል። |
እግዚአብሔር ጠባቂዬና መከታዬ ነው፤ መጠለያዬና አዳኜ ነው፤ በእርሱ ተማምኜ በሰላም እኖራለሁ፤ እርሱ አሕዛብን ከእግሬ በታች አድርጎ ያስገዛልኛል።
ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ እንደ ፀሐይና እንደ ጋሻ ነህ፤ በቸርነትና በክብር ትጠብቀናለህ፤ ደግ ለሚሠሩ ሰዎች ማናቸውንም መልካም ነገር አትከለክላቸውም።
እናንተን ግን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አደረገ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ጥበባችን፥ ጽድቃችን፥ ቅድስናችንና ቤዛችን እንዲሆን አደረገው።