ምሳሌ 16:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የንጉሥ ቊጣ የሞት መልእክተኛ ነው። ብልኅ ሰው ግን ቊጣውን ያበርዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሥ ቍጣ የሞት መልእክተኛ ነው፤ ጠቢብ ሰው ግን ቍጣውን ያበርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጉሥ ቁጣ እንደ ሞት መልእክተኛ ነው፥ ጠቢብ ሰው ግን ያቈላምጠዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንጉሥ ቍጣ እንደ መልአከ ሞት ነው፤ ብልህ ሰው ግን ያቈላምጠዋል። |
ንጉሡም እጅግ ተቈጣና ግብዣውን ትቶ በመነሣት ከነበረበት ክፍል ወጥቶ ወደ ቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ ሄደ፤ ንጉሡ በዚህ ጥፋት ሊቀጣው የወሰነ መሆኑን ሃማን ተገንዝቦ ስለ ነበር ሕይወቱን ታተርፍለት ዘንድ ንግሥት አስቴርን ለመማጠን ወደ ኋላ ቀረ።
ስለዚህ ንጉሡ ወዲያውኑ አንዱን የዘብ ጠባቂ ወታደር የዮሐንስን ራስ ቈርጦ እንዲያመጣ ላከው፤ ወታደሩም ወደ ወህኒው ቤት ሄዶ የዮሐንስን ራስ ቈረጠ፤
ሄሮድስ በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ላይ በጣም ተቈጥቶ ነበር፤ እነርሱም በአንድነት መጡና፤ የንጉሥ ባለሟል ብላስጦስ እንዲተባበራቸው ለምነው እሺ ካሰኙትም በኋላ ንጉሡን ዕርቅ ጠየቁ፤ ይህንንም ያደረጉት አገራቸው ምግብ የምታገኘው ከንጉሡ ግዛት ስለ ነበረ ነው።
እግዚአብሔር ሰዎችን በእኛ አማካይነት ስለሚጠራ እኛ የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን፤ ስለዚህ “ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ!” ብለን በክርስቶስ ስም እንለምናችኋለን።