Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 29:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ለሌሎች ሰዎች ደንታ የሌላቸው ፌዘኞች በከተማ ውስጥ ብጥብጥ ያነሣሣሉ፤ ጠቢባን ግን የደፈረሰውን ጸጥታ መልሰው ያረጋጋሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ተሳዳቢዎች ከተማን ያውካሉ፤ ጠቢባን ግን ቍጣን ያበርዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ፌዘኞች ከተማቸውን ያቃጥላሉ፥ ጠቢባን ግን ቁጣን ያስቀራሉ።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 29:8
19 Referencias Cruzadas  

በእውነተኞች ሰዎች በረከት ምክንያት ከተማ እያደገች ትሄዳለች፤ የክፉ ሰዎች መጥፎ ንግግር ግን ወደ ውድቀት ያደርሳታል።


ልዝብ አነጋገር ቊጣን ያስታግሣል፤ የቊጣ አነጋገር ግን ቊጣን ያባብሳል።


የንጉሥ ቊጣ የሞት መልእክተኛ ነው። ብልኅ ሰው ግን ቊጣውን ያበርዳል።


ጥበበኛ ሰው ሞኝን ሰው ከሶ ፍርድ ቤት ቢያቀርብ ሞኙ ሰው በቊጣና በሳቅ ሰላምን ይነሣል።


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል እንኳ በፊቴ ቆመው ቢማልዱ ለዚህ ሕዝብ ምሕረት አላደርግም፤ ስለዚህ ከፊቴ ወዲያ እንዲሄዱ አድርግ።


በቊጣዬ አገሪቱን ከማጥፋቴ በፊት የቅጽር ግንብ የሚሠራ፥ ቅጽሮቹ በፈረሱበት በኩል በመቆም በእኔና በሕዝቡ መካከል ገብቶ ቊጣዬን የሚያበርድ ሰው ፈለግኹ፤ ነገር ግን ማንንም አላገኘሁም።


በዚህም መቅሠፍቱ እንዲቆም አደረገ፤ አሮንም በሞቱትና በሕይወት ባሉት መካከል ቆሞ ነበር።


“የካህኑ የአሮን የልጅ ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ባደረገው ነገር ምክንያት በእስራኤል ሕዝብ ላይ ያለኝ ቊጣ በርዶአል፤ ፊንሐስ ከእኔ በቀር ለሌላ አምላክ የሚሰግዱትን መታገሥ አልፈለገም፤ በቊጣዬ እስራኤልን ያላጠፋሁትም እርሱ ስለ እኔ ባሳየው ቅናት ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos