Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አስቴር 7:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ንጉሡም እጅግ ተቈጣና ግብዣውን ትቶ በመነሣት ከነበረበት ክፍል ወጥቶ ወደ ቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ ሄደ፤ ንጉሡ በዚህ ጥፋት ሊቀጣው የወሰነ መሆኑን ሃማን ተገንዝቦ ስለ ነበር ሕይወቱን ታተርፍለት ዘንድ ንግሥት አስቴርን ለመማጠን ወደ ኋላ ቀረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ንጉሡ ከተቀመጠበት በቍጣ ተነሣ፤ የወይን ጠጁንም ትቶ ወደ ቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ ሄደ። ሐማ ግን ንጉሡ ሊያጠፋው ቈርጦ መነሣቱን ስላወቀ፣ ንግሥት አስቴር ሕይወቱን እንድታተርፍለት ለመማጠን በዚያው ቀረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ንጉሡም ተቈጥቶ የወይን ጠጅ ከመጠጣቱ ተነሣ፥ ወደ ንጉሡም ቤት አታክልት ውስጥ ሄደ። ሐማም ከንጉሡ ዘንድ ክፉ ነገር እንደ ታሰበበት አይቶአልና ከንግሥቲቱ ከአስቴር ሕይወቱን ይለምን ዘንድ ቆመ።

Ver Capítulo Copiar




አስቴር 7:7
14 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ይህን የንጉሡን ትእዛዝ ለንግሥት አስጢን በነገሩአት ጊዜ ወደ ንጉሡ ፊት ለመቅረብ እምቢ አለች፤ ይህም ሁኔታ ንጉሡን እጅግ አስቈጣው።


ከዚህም በኋላ ንጉሥ አርጤክስስ የመናገሻ ከተማ በሆነችው በሱሳ ለሚኖሩ ሁሉ ለሀብታሞችም፥ ለድኾችም፥ እንደገና ሌላ ግብዣ አደረገ፤ በቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ ውስጥ የተደረገውም ያ ግብዣ አንድ ሳምንት ሙሉ ቈየ።


ስለዚህም ሃማን መርዶክዮስን ለመስቀል ባዘጋጀው እንጨት ላይ ተሰቀለ፤ ከዚያም በኋላ የንጉሡ ቊጣ በረደ።


ክፉዎች ይህን አይተው ይቈጣሉ፤ ተስፋ በመቊረጥም ጥርሳቸውን ያፋጫሉ፤ የክፉዎችም ምኞት ከንቱ ይሆናል።


ክፉዎች በደጋግ ሰዎች ፊት ይንበረከካሉ፤ ኃጢአተኞች በጻድቃን ደጅ ያጐነብሳሉ።


ነገሥታት ችሎታ ባላቸው አገልጋዮች ይደሰታሉ፤ አሳፋሪ አገልጋዮች ግን ንጉሡን ያስቈጣሉ።


የንጉሥ ቊጣ የሞት መልእክተኛ ነው። ብልኅ ሰው ግን ቊጣውን ያበርዳል።


የንጉሥ ቊጣ እንደ አንበሳ ጩኸት አስፈሪ ነው፤ ከንጉሥ ዘንድ የሚገኝ ሞገስ ግን ሣርን እንደሚያለመልም ጠል ነው።


የጨቋኞችሽ የልጅ ልጆች ወደ አንቺ ሲመጡ እጅ ይነሣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ በእግርሽ ሥር ይንበረከካሉ፤ እነርሱም አንቺን “የእስራኤል ቅዱስ የእግዚአብሔር ከተማ የሆነችው ጽዮን” ብለው ይጠሩሻል።


በዚያን ጊዜ ናቡከደነፆር በሲድራቅ፥ በሚሳቅና በአብደናጎ ላይ እጅግ ተቈጥቶ መልኩ ተለዋወጠ፤ ስለዚህ እሳቱ ከቀድሞው ይበልጥ በሰባት እጥፍ ከፍ ብሎ እንዲነድ ትእዛዝ ሰጠ።


እንግዲህ፥ አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን የሚሉትን እነዚያን ከሰይጣን ማኅበር የሆኑትን ውሸታሞች መጥተው በእግርህ ሥር እንዲወድቁ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኩህም እንዲያውቁ አደርጋቸዋለሁ።


ንጉሡም ‘እሺ’ ቢል፥ እኔ አገልጋይህ በሰላም እንደምኖር ዐውቃለሁ፤ ንጉሡ ከተቈጣ ግን ጒዳት ሊያደርስብኝ የወሰነ መሆኑን ታውቃለህ፤


ዮናታን ግን “እንዲህ ያለውን ነገር ፈጽሞ አታስብ! በአንተ ክፉ ነገር አስቦ ቢሆን ኖሮ፥ እነግርህ አልነበረም?” አለው።


እባክሽን ይህን ጉዳይ አስቢበትና ማድረግ ስለሚገባሽ ነገር ወስኚ፤ አለበለዚያ ለጌታችንና ለቤተሰቡ ሁሉ አደገኛ ጥፋት ይሆናል፤ እርሱ እንደ ሆነ የማንንም ምክር የማይሰማ ደረቅ ሰው ነው!”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos