አስቴር 7:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ምሕረትም ለመለመን አስቦ ንግሥት አስቴር በተቀመጠችበት ድንክ አልጋ ላይ በግንባሩ ተደፋ፤ ንጉሡም ከአትክልቱ ቦታ ተመልሶ ወደ ክፍሉ በገባ ጊዜ ይህን በማየቱ እጅግ ተቈጥቶ “ይህ ሰው በገዛ ቤተ መንግሥቴ ዐይኔ እያየ ንግሥቲቱን ሊደፍር ይፈልጋል እንዴ?” ሲል ጮኸበት። ንጉሡም ገና ይህን እንደ ተናገረ ወዲያውኑ ጃንደረቦቹ የሃማንን ፊት ሸፈኑ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ንጉሡ ከቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ ወደ ግብዣው አዳራሽ ሲመለስ አስቴር ደገፍ ባለችበት ድንክ ዐልጋ ላይ ሐማ ተደፍቶ ነበር። ንጉሡም፣ “ይባስ ብሎ ዐብራኝ ያለችውን ንግሥት በገዛ ቤቴ ሊደፍራት ያስባልን?” ሲል ተናገረ። ይህ ቃል ከንጉሡ አፍ ገና እንደ ወጣ፣ የሐማን ፊት ሸፈኑት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ንጉሡም ከቤቱ አታክልት ወደ ወይን ጠጁ ግብዣ ስፍራ ተመለሰ፥ ሐማም አስቴር ባለችበት አልጋ ላይ ወድቆ ነበር። ንጉሡም፦ ደግሞ በቤቴ በእኔ ፊት ንግሥቲቱን ይጋፋታልን? አለ። ይህም ቃል ከንጉሡ አፍ በወጣ ጊዜ የሐማን ፊት ሸፈኑት። Ver Capítulo |