ምሳሌ 14:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገሥታት ችሎታ ባላቸው አገልጋዮች ይደሰታሉ፤ አሳፋሪ አገልጋዮች ግን ንጉሡን ያስቈጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠቢብ አገልጋይ ንጉሥን ደስ ያሰኛል፤ አሳፋሪ አገልጋይ ግን ቍጣውን በራሱ ላይ ያመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስተዋይ አገልጋይ በንጉሥ ዘንድ ይወደዳል፥ በሚያሳፍር ላይ ግን ቁጣው ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አስተዋይ መልእክተኛ በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ነው፤ በመልካም ጠባዩም ውርደትን ከራሱ ያርቃል። |
ንጉሡም እጅግ ተቈጣና ግብዣውን ትቶ በመነሣት ከነበረበት ክፍል ወጥቶ ወደ ቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ ሄደ፤ ንጉሡ በዚህ ጥፋት ሊቀጣው የወሰነ መሆኑን ሃማን ተገንዝቦ ስለ ነበር ሕይወቱን ታተርፍለት ዘንድ ንግሥት አስቴርን ለመማጠን ወደ ኋላ ቀረ።
ጌታውም ‘መልካም አደረግህ፤ አንተ ታማኝና ደግ አገልጋይ! በጥቂት ነገር ታማኝ ሆነህ ስለ ተገኘህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ና የጌታህን ደስታ ለመካፈል ግባ!’ አለው።
ጌታውም ‘መልካም ነው! አንተ ታማኝና መልካም አገልጋይ በጥቂት ነገር ታማኝ ሆነህ ስለ ተገኘህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ና የጌታህን ደስታ ለመካፈል ግባ!’ አለው።