ምሳሌ 11:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጻድቅ ሰው ሥራ የዘለዓለም ሕይወትን ያስገኛል፤ ዐመፅ ግን ለሕይወት መጥፋት ምክንያት ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ናት፤ ነፍሳትን የሚማርክም ጠቢብ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ናት፥ ነፍሶችንም የሚማርክ እርሱ ጠቢብ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ይወጣል። የዐመፀኞች ነፍሳት ግን በድንገት ይወገዳሉ። |
በዚያን ጊዜ ጠቢባን እንደ ሰማይ ብርሃን ያንጸባርቃሉ፤ ብዙ ሰዎችን በማስተማር ከክፉ መንገድ ወደ ደግ ሥራ የመለሱ ሁሉ ለዘለዓለም እንደ ሰማይ ከዋክብት ያበራሉ።”
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ! ‘ድል ለሚነሣ በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ካለው ከሕይወት ዛፍ ፍሬ እንዲበላ አደርገዋለሁ።’