አንተ የሰውን ሁሉ ልብ ፈትነህ፥ ታማኝ በሆነ ሕዝብ እንደምትደሰት ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም እኔ ይህን ሁሉ በፈቃዴ ለአንተ የሰጠሁት፥ በታማኝነትና በቅንነት ነው፤ ደግሞም እዚህ የተሰበሰበው ሕዝብህ ለአንተ ስጦታ በማቅረቡ፥ እጅግ መደሰቱን ተገንዝቤአለሁ፤
ምሳሌ 11:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ልበ ጠማሞችን ይጸየፋል። ነቀፋ በሌለበት መንገድ በሚሄዱ ሰዎች ይደሰታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ልበ ጠማሞችን ይጸየፋል፤ በመንገዳቸው ነቀፋ በሌለባቸው ሰዎች ግን ደስ ይሰኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልበ ጠማሞች በጌታ ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው፥ በመንገዳቸው ፍጹማን የሆኑ ግን የተወደዱ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠማማ መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ በመንገዳቸው ፍጹማን የሆኑ ግን በፊቱ የተመረጡ ናቸው። |
አንተ የሰውን ሁሉ ልብ ፈትነህ፥ ታማኝ በሆነ ሕዝብ እንደምትደሰት ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም እኔ ይህን ሁሉ በፈቃዴ ለአንተ የሰጠሁት፥ በታማኝነትና በቅንነት ነው፤ ደግሞም እዚህ የተሰበሰበው ሕዝብህ ለአንተ ስጦታ በማቅረቡ፥ እጅግ መደሰቱን ተገንዝቤአለሁ፤