ምሳሌ 10:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን እንዲራቡ አያደርግም፤ ክፉዎች ግን የተመኙትን እንዳያገኙ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ጻድቁ እንዲራብ አያደርግም፤ የክፉዎችን ምኞት ግን ያጨናግፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ የጻድቁን ነፍስ አያስርብም፥ የክፉዎችን ምኞት ግን ይገለብጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ጻድቅት ነፍስን አያስርብም፤ የኃጥኣንን ሕይወት ግን ከምድር ያስወግዳል። |
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ችግርንና ጭንቀትን አይተህ ልታስወግዳቸው መፍትሔ ታዘጋጃለህ፤ ችግረኛ ራሱን ለአንተ ይሰጣል፤ አንተም የሙት ልጆችን ትረዳለህ።
እግዚአብሔር ቊጣውን በሚገልጥበት በዚያን ቀን ሰዎችን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እንደ እሳት ባለው ቅናቱ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ ይህም የሚሆነው በዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በድንገት የሚያልቁ ስለ ሆነ ነው።