እግዚአብሔርም “ሕይወት ሰጪ የሆነ መንፈሴ ከሰዎች ጋር ለዘለዓለም አይኖርም፤ ሰዎች ሟቾች ስለ ሆኑ ከእንግዲህ ወዲያ ከ 120 ዓመት የበለጠ አይኖሩም” አለ።
ምሳሌ 1:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ እኔን ጥበብን ትጣራላችሁ፤ እኔ ግን አልመልስላችሁም፤ በየቦታውም ትፈልጉኛላችሁ፤ ነገር ግን አታገኙኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚያ ጊዜ ይጠሩኛል፤ እኔ ግን አልመልስላቸውም፤ አጥብቀው ይፈልጉኛል፤ ነገር ግን አያገኙኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፥ እኔ ግን አልመልስም፥ ተግተው ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግን በጠራችሁኝ ጊዜ እኔ አልሰማችሁም፤ ክፉዎች ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም። |
እግዚአብሔርም “ሕይወት ሰጪ የሆነ መንፈሴ ከሰዎች ጋር ለዘለዓለም አይኖርም፤ ሰዎች ሟቾች ስለ ሆኑ ከእንግዲህ ወዲያ ከ 120 ዓመት የበለጠ አይኖሩም” አለ።
ለውዴ በሩን ከፈትኩለት። ውዴ ደርሶ ተመለሰ፤ ድምፁን ለመስማት እጅግ ጓጉቼ ነበር፤ አጥብቄ ፈለግኹት፤ ነገር ግን ላገኘው አልቻልኩም፤ ጠራሁት፤ እርሱ ግን አልመለሰልኝም።
“እጆቻችሁን ወደ እኔ ለጸሎት ብትዘረጉ፥ ወደ እናንተ አልመለከትም፤ እጆቻችሁ በደም የተበከሉ ስለ ሆኑ የቱንም ያኽል ልመና ብታበዙ አልሰማችሁም፤
ስለዚህም እነሆ እኔ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤ ከጥፋቱም ማምለጥ አይችሉም፤ የእኔን ርዳታ ለማግኘት ቢጮኹም እንኳ አልሰማቸውም።
እየጾሙ ቢጸልዩ እንኳ አላዳምጣቸውም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም ሆነ የእህል ቊርባን ቢያቀርቡልኝ እንኳ በእነርሱ ደስ አልሰኝም፤ ይልቁንም በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ እንዲያልቁ አደርጋለሁ።”
መሥዋዕት አድርገው ለማቅረብ በጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን ነድተው እግዚአብሔርን ለመፈለግ ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ስለ ተለያቸው አያገኙትም።
እናንተም ተጨንቃችሁ ወደ እግዚአብሔር የምትጮኹበት ጊዜ ይመጣል፤ ነገር ግን እርሱ አይመልስላችሁም፤ ክፉ ሥራ ስለ ሠራችሁ ልመናችሁ አይሰማም።”
ያ ዘመን በደረሰ ጊዜ የመረጣችሁት ንጉሥ ስለሚፈጽምባችሁ በደል በመረረ ሁኔታ ማጒረምረም ትጀምራላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን አቤቱታችሁን አያዳምጥም።”