ዘኍል 9:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን በምሽት በሲና ምድረ በዳ በዓሉን አከበሩ፤ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሁሉን ነገር አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም በመጀመሪያው ወር፣ በዐሥራ አራተኛውም ቀን ፀሓይ በምትጠልቅበት ጊዜ በሲና ምድረ በዳ ፋሲካ አደረጉ፤ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሁሉንም አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጀመሪያውም ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በሲና ምድረ በዳ የፋሲካን በዓል አከበሩ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጀመሪያውም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን በሲና ምድረ በዳ ፋሲካን አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጀመሪያውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በሲና ምድረ በዳ ፋሲካን አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉ። |
ግብጽን ለቀው ከወጡ በኋላ አርባኛው ዓመት በገባ በዐሥራ አንደኛው ወር መጀመሪያ ቀን ሙሴ ለሕዝቡ ያስረዳቸው ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘውን ቃል ሁሉ ነገራቸው።
“እግዚአብሔር አምላኬ እንድነግራችሁ ያዘዘኝን ሕግና ሥርዓት ሁሉ አስተምሬአችኋለሁ፤ እርስዋን ለመውረስ በምትገቡባት ምድር ስትኖሩ እነዚህን ትእዛዞች አክብሩ።
አብርሃም ወጥቶ ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ ምንም እንኳ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ለመሄድ የታዘዘው በእምነት ነው።