ዘኍል 9:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቀን ደመና ይሸፍነው ነበር፤ ደመናውም በሌሊት እንደ እሳት ያበራ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ በዚህ ሁኔታ ቀጠለ፤ ደመናው ማደሪያውን ሸፈነው፤ በሌሊትም የእሳት መልክ ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁልጊዜ በማደርያው ላይ እንዲሁ ነበረ፤ በቀን ደመና በሌሊትም የእሳት አምሳል ይሸፍነው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁ ሁልጊዜ ነበረ፤ በቀን ደመና፥ በሌሊትም የእሳት አምሳል ይሸፍናት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ ሁልጊዜ ነበረ፤ በቀን ደመና በሌሊትም የእሳት አምሳል ይሸፍነው ነበር። |
ምሕረትህም ታላቅ በመሆኑ በዚያ ምድረ በዳ ይጠፉ ዘንድ አልተውካቸውም፤ ነገር ግን የደመናው ዐምድ በቀን ይመራቸው ነበር፤ የእሳቱ ዐምድ በሌሊት ያበራላቸው ነበር።
ይህም እግዚአብሔር በክርስቶስ የዓለምን ሰዎች ሁሉ ከራሱ ጋር አስታረቀ ማለት ነው፤ በደላቸውንም አልቈጠረባቸውም፤ ለእኛም ሰውን ከጌታ ጋር የምናስታርቅበትን ቃል ሰጠን።
እንዲህም የሚል ከፍተኛ ድምፅ ከዙፋኑ ሲወጣ ሰማሁ፤ “እነሆ! የእግዚአብሔር ማደሪያ ከሰዎች ጋር ነው፤ ከእነርሱም ጋር ይኖራል፤ እነርሱም የእርሱ ሕዝብ ይሆናሉ። እግዚአብሔር ራሱ ከእነርሱ ጋር ይሆናል፤ አምላካቸውም ይሆናል፤