Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 5:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ይህም እግዚአብሔር በክርስቶስ የዓለምን ሰዎች ሁሉ ከራሱ ጋር አስታረቀ ማለት ነው፤ በደላቸውንም አልቈጠረባቸውም፤ ለእኛም ሰውን ከጌታ ጋር የምናስታርቅበትን ቃል ሰጠን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋራ ሲያስታርቅ የሰዎችን በደል አይቈጥርባቸውም ነበር፤ ለእኛም ደግሞ የማስታረቅ ቃል ሰጠን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ይህ እግዚአብሔር የሰዎችን በደል ሳይቆጥርባቸው በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር አስታርቋል፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኑሯል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይቅር ብሎ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ሳያ​ስብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በክ​ር​ስ​ቶስ ዓለ​ሙን ከራሱ ጋር አስ​ታ​ር​ቆ​አ​ልና፤ የዕ​ርቅ ቃሉ​ንም በእኛ ላይ አደ​ረገ፤ የይ​ቅ​ር​ታ​ው​ንም መል​እ​ክት ሰጠን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 5:19
16 Referencias Cruzadas  

ይህም ሁሉ ሆኖ ኃጢአታችሁን ይቅር የምል አምላክ እኔ ነኝ፤ ይህንንም የማደርገው ስለ እናንተ ሳይሆን ስለ እኔነቴ ነው፤ ስለዚህ ኃጢአታችሁን አልቈጥርባችሁም።


በደልህን እንደ ደመና ኃጢአትህን እንደ ማለዳ ጭጋግ አስወግጄአለሁ፤ ስለ አዳንኩህ ወደ እኔ ተመለስ።”


በቀን ደመና ይሸፍነው ነበር፤ ደመናውም በሌሊት እንደ እሳት ያበራ ነበር።


“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙም ‘ዐማኑኤል’ ተብሎ ይጠራል።” ዐማኑኤል ማለትም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው።


እኔ በአብ እንዳለሁ፥ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ፥ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።


እኔ የምለምነው እኔ በእነርሱ አንተም በእኔ እንደ ሆንክ እነርሱም በፍጹም አንድ እንዲሆኑ ነው፤ እንዲሁም እኔን እንደ ላክኸኝና እኔን በወደድከኝ መጠን እነርሱንም እንደ ወደድካቸው ዓለም እንዲያውቅ ነው።


እግዚአብሔር እነርሱን በጣላቸው ጊዜ ሌላው የዓለም ሕዝብ ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቀ እግዚአብሔር እነርሱን በሚቀበላቸው ጊዜ ምን የሚሆን ይመስላችኋል? ይህማ ከሞት እንደ መነሣት ያኽል ነው!


ፍቅር ሥርዓተቢስ አያደርግም፤ ፍቅር ያለው ሰው የራሱን ጥቅም ብቻ አይፈልግም፤ ፍቅር ያለው ሰው አይበሳጭም፤ ፍቅር ያለው ሰው ቢበደልም በደልን እንደ በደል አይቈጥርም፤


የአምላክነት ፍጹም ሙላት በአካል ተገልጦ የሚኖረው በክርስቶስ ነው።


የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር፦ “ሰው ሆኖ ተገለጠ፤ እውነተኛነቱ በመንፈስ ታወቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ ለሕዝቦች ሁሉ ተሰበከ፥ በዓለም ያሉ ሰዎች አመኑበት፥ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ” የሚል ነው።


ፍቅር ማለት እንዲህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን ስለ ወደድነው ሳይሆን እርሱ ስለ ወደደንና ኃጢአታችንን እንዲደመስስ ልጁን ስለ ላከልን ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos