Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 40:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 በሚጓዙበት ጊዜ ሁሉ በቀን የእግዚአብሔርን ክብር የሚገልጠው ደመና ድንኳኑን ሲሸፍን፥ በሌሊት ደግሞ በደመናው ውስጥ እሳት ያዩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ስለዚህ በጕዟቸው ሁሉ ወቅት፣ በእስራኤል ቤት ፊት ሁሉ የእግዚአብሔር ደመና በቀን ከማደሪያው በላይ፣ በሌሊትም እሳቱ በደመናው ውስጥ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 በጉዞአቸው ሁሉ በእስራኤል ቤት ሁሉ ፊት የጌታ ደመና በቀን በማደሪያው ላይ፥ በሌሊትም እሳት በዚያ ላይ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ደመና በቀን በድ​ን​ኳኑ ላይ ነበ​ርና፥ እሳ​ቱም በሚ​ጓ​ዙ​በት ሁሉ በሌ​ሊት በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት በእ​ር​ስዋ ላይ ነበ​ርና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 በመንገዳቸውም ሁሉ በእስራኤል ቤት ሁሉ ፊት የእግዚአብሔር ደመና በማደሪያው ላይ በቀን ነበረና፥ እሳትም በሌሊት በዚያ ላይ ነበረና።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 40:38
10 Referencias Cruzadas  

የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ በመታደግ ካዳንኩበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ በድንኳን ውስጥ ሆኜ በየስፍራው ስዘዋወር ኖርኩ እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርኩም፤


በሚሄዱበትም ጊዜ በደመና ጋረዳቸው፤ በሌሊትም፥ ብርሃን የሚሰጣቸውን እሳት አዘጋጀላቸው።


ቀን በደመና፥ ሌሊት በእሳት ብርሃን መራቸው።


ቀንና ሌሊት መጓዝ ይችሉ ዘንድ፥ እግዚአብሔር ቀን በደመና ዐምድ፥ ሌሊት ደግሞ ብርሃን በሚሰጥ በእሳት ዐምድ ይመራቸው ነበር፤


በዚህ ዐይነት የደመናው ዐምድ በቀን፥ የእሳቱ ዐምድ በሌሊት ዘወትር እፊት እፊታቸው ይገኝ ነበር።


ከእያንዳንዱ ሰፈር ሲለቁ የእግዚአብሔር ደመና በቀን ይጋርዳቸው ነበር።


እስከ ማግስቱ ጠዋት ድረስ ከዚያ ምግብ አስተርፈው አያሳድሩ፤ ከእንስሳውም አጥንት አንዱንም አይስበሩ፤ በተሰጣቸው የሥርዓት መመሪያ መሠረት በዓሉን ያክብሩ፤


የመገናኛው ድንኳን በተተከለበት ቀን ደመናው ድንኳኑን ሸፈነው፤ ከማታ ጀምሮ እስከ ጠዋት ድረስ በድንኳኑ ላይ እንደ እሳት ያበራ ነበር፤


በቀን ደመና ይሸፍነው ነበር፤ ደመናውም በሌሊት እንደ እሳት ያበራ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos