ዘኍል 7:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያቀረባቸውም መባዎች እነዚህ ናቸው፦ በመቅደሱ ሚዛን መሠረት መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን አንድ ከብር የተሠራ ዝርግ ሳሕን፥ ከሰባ ሰቅል ብር የተሠራ አንድ ጐድጓዳ ሳሕን፥ ሁለቱም ለእህል ቊርባን በሚሆን ከዘይት ጋር በተቀላቀለ ደቃቅ ዱቄት የተሞሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መባውም ለእህል ቁርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ጐድጓዳ ሳሕን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መባውም ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መባውም ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤ |
ድስቶቹ፥ መጫሪያዎቹና ጐድጓዳ ሳሕኖቹ፤ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሑራም እነዚህን ሁሉ ዕቃዎች ለሰሎሞን የሠራለት ከተወለወለ ንጹሕ ነሐስ ነበር።
ከዚህ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ፥ አማካሪዎቹ፥ ባለሟሎቹና በዚያ የተገኙት እስራኤላውያን ለቤተ መቅደስ መገልገያ ይሆን ዘንድ የሰጡትን ብር፥ ወርቅና ሌሎቹንም ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ በሚዛን መዝኜ ለእነዚህ ካህናት አስረከብኳቸው።
ከሕዝብ ቈጠራ ውስጥ የሚገባ እያንዳንዱ ሰው በተቀደሰው ድንኳን በታወቀው ሚዛን ልክ አንድ ጥሬ ብር ይክፈል፤ እያንዳንዱ ሰው ይህን ለእግዚአብሔር መባ አድርጎ ያቅርብ፤
በጠረጴዛው ላይ የሚቀመጡ ልዩ ልዩ የመገልገያ ዕቃዎችን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ፤ ይኸውም፦ የዕጣን ማስቀመጫ ዝርግ ሳሕኖችንና ወጭቶችን፥ ጭልፋዎችን ለወይን ጠጅ መቅጃ የሚሆኑ ማንቈርቈሪያዎችንና ጐድጓዳ ሣሕኖችን ሠራ።
የክብር ዘቡ አዛዥ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፥ የዕጣን ማጠኛዎችን፥ ጐድጓዳ ወጭቶችን፥ ድስቶችን፥ መቅረዞችን፥ ጭልፋዎችን፥ የመጠጥ መሥዋዕት ማቅረቢያዎችን፥ በወርቅና በብር የተሠሩ ዕቃዎችን ሁሉ ወሰደ።
የወይን ጠጅ እየጠጡ ሳለ ብልጣሶር ሞቅ ባለው ጊዜ አባቱ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ያመጣቸውን ከወርቅና ከብር የተሠሩ ጽዋዎችን እንዲያመጡ አገልጋዮቹን አዘዘ፤ ንጉሡ ይህን ያደረገው እርሱና መኳንንቱ፥ ሚስቶቹና ቁባቶቹ በእነዚያ የወርቅ ጽዋዎች እንዲጠጡባቸው ፈልጎ ነው።
በዚያን ጊዜ በፈረሶች አንገት ላይ በሚንጠለጠል ቃጭል ሁሉ ላይ “ለእግዚአብሔር የተለየ” የሚል የጽሕፈት ምልክት ይቀረጽበታል፤ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያለው የማብሰያ ማሰሮ በመሠዊያው ላይ እንደሚገኘው ሳሕን የተቀደሰ ይሆናል።
እንግዲህ እንደዚህ ያለውን መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ሁሉ በሩብ ሊትር ዘይት የተለወሰ አንድ ኪሎ ምርጥ ዱቄት የእህል ቊርባንም ማቅረብ አለበት፤
ይህንንም ሁሉ መሥዋዕት በየወሩ መጀመሪያ ቀን ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቊርባን፥ እንዲሁም በየቀኑ ከሚቀርበው መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ ከሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት የእህል ቊርባንና የመጠጥ መባ ጋር ተጨማሪ በማድረግ ታቀርባላችሁ፤ ይህም የምግብ ቊርባን ይሆናል።