ካህኑ ሳዶቅም እዚያው ነበር፤ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ሌዋውያን ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ የቃል ኪዳኑን ታቦት፥ ሕዝቡ ሁሉ ከተማውን ለቆ እስኪወጣ ድረስ በአብያታር አጠገብ አስቀመጡት።
ዘኍል 4:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰፈር በሚነሡበትም ጊዜ አሮንና ልጆቹ ንዋያተ ቅድሳቱንና የእነርሱንም መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ የቀዓት ልጆች መጥተው ይሸከሙአቸው፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ ንዋያተ ቅድሳቱን መንካት አይገባቸውም፤ እንግዲህ የመገናኛው ድንኳን በሚነሣበት ጊዜ ሁሉ የቀዓት ልጆች ኀላፊነት ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና ዕቃዎቹን፣ ንዋየ ቅድሳቱንም በሙሉ ሸፍነው ከጨረሱ በኋላ ሰፈሩ ለመንቀሳቀስ ዝግጁ ሲሆን፣ ቀዓታውያን ለመሸከም ይምጡ፤ እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን መንካት የለባቸውም፤ ስለዚህ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያሉትን እነዚህን ዕቃዎች የሚሸከሙ ቀዓታውያን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃዎች ሁሉ መሸፈናቸውን በጨረሱ ጊዜ፥ ሰፈሩም ለመጓዝ ሲነሣ፥ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ከዚያም በኋላ ይመጣሉ፤ እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። የቀዓት ልጆች የሚሸከሙአቸው የመገናኛው ድንኳን ዕቃዎች እነዚህ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍነው ከጨረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ይገባሉ። እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። በምስክሩ ድንኳን ዘንድ የቀዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰፈሩም ሲነሡ፥ አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃ ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ይመጣሉ፤ እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። በመገናኛው ድንኳን ዘንድ የቀዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው። |
ካህኑ ሳዶቅም እዚያው ነበር፤ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ሌዋውያን ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ የቃል ኪዳኑን ታቦት፥ ሕዝቡ ሁሉ ከተማውን ለቆ እስኪወጣ ድረስ በአብያታር አጠገብ አስቀመጡት።
የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ሰዎች ስድስት እርምጃ በተራመዱ ቊጥር ዳዊት እንደገና እያስቆመ አንድ ወይፈንና አንድ የሰባ ፍሪዳ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርብ ነበር።
ከዚህም በኋላ ዳዊት እግዚአብሔር ለዘለዓለም እርሱን እንዲያገለግሉና የቃል ኪዳኑንም ታቦት እንዲሸከሙ የመረጣቸው እነርሱን ስለ ሆነ “የቃል ኪዳኑን ታቦት መሸከም የሚገባቸው ሌዋውያን ብቻ ናቸው” አለ።
ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔር የሚመለክበትን ድንኳንና ለአምልኮ ሥነ ሥርዓት መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች ሌዋውያን መሸከም አይኖርባቸውም።”
በተራራው ዙሪያ ድንበር አብጅ፤ እነርሱም ያንን ድንበር አልፈው ወደ ተራራው እንዳይወጡና እንዲያውም ድንበሩን እንዳይነኩ ንገራቸው፤ ማንም ሰው ከተወሰነው ድንበር አልፎ፥ ተራራውን ቢነካ በሞት ይቀጣ፤
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔን እግዚአብሔርን ለማየት የተወሰነውን ክልል አልፈው እንዳይመጡ ወርደህ ለሕዝቡ ንገር፤ ይህን ቢያደርጉ ግን ከእነርሱ ብዙዎቹ ይሞታሉ፤
በዚህ ፈንታ ሌዋውያንን በመገናኛው ድንኳንና በውስጡም ባሉት የመገልገያ ዕቃዎች ላይ ኀላፊዎች አድርገህ መድባቸው፤ እነርሱ ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ይሸከማሉ፤ በድንኳኑም ውስጥ ያገለግላሉ፤ በዙሪያውም ይሰፍራሉ።
ሰፈራችሁን ለቃችሁ በምትሄዱበት ጊዜ ሌዋውያን ብቻ ድንኳኑን ነቅለው በሚሰፍሩበት አዲስ ቦታ ይተክሉታል፤ ከእነርሱ በቀር ወደ ድንኳኑ የሚቀርብ ማንኛውም ሰው በሞት ይቀጣል።
ከዚህ በኋላ የሌዋዊው የቀዓት ጐሣ የሆኑት ሰዎች ንዋያተ ቅድሳትን ተሸክመው ተጓዙ፤ እነርሱ ወደሚቀጥለው ሰፈር ከመድረሳቸው በፊት ድንኳኑ እንደገና መተከል ነበረበት።
እነርሱም እናንተን የመርዳት ተግባራቸውን እያከናወኑ ድንኳኑንም የመንከባከብ ኀላፊነት ይወስዳሉ፤ ይሁን እንጂ በተቀደሰው ስፍራና በመሠዊያው ላይ ያሉትን ንዋያተ ቅድሳት መንካት አይኖርባቸውም፤ ነክተው ቢገኙ ግን እነርሱም እናንተም በአንድነት ትሞታላችሁ።
በመገናኛው ድንኳን በስተምሥራቅ፥ በፀሐይ መውጫ በኩል የሚሰፍሩት ሙሴ አሮንና የአሮን ልጆች ነበሩ፤ በመቅደሱ ውስጥ ስለ እስራኤል ሕዝብ ለሚፈጸም ማንኛውም ዐይነት የአገልግሎት ሥነ ሥርዓት ኀላፊዎች እነርሱ ነበሩ፤ ማንም ሌላ ሰው ወደ መቅደሱ ቢቀርብ በሞት ይቀጣል።
በመሠዊያው ላይ ለማገልገል የሚጠቅሙትን ዕቃዎች፥ ማለትም ማንደጃዎችን፥ ሜንጦዎችን፥ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን ያስቀምጡበት፤ የተለፋውንም ስስ ቊርበት በላዩ ደርበው መሎጊያዎችን ያስገቡበት።
ወደ ተቀደሰው ስፍራ ተጠግተው እንዳይሞቱ እንዲህ አድርግላቸው፦ አሮንና ልጆቹ ወደ መቅደሱ ገብተው የያንዳንዱን ሰው ሥራና ሸክሙን ይመድቡለት።
በእነርሱ ኀላፊነት የሚጠበቁት ንዋያተ ቅድሳት በትከሻቸው የሚሸከሙአቸው ስለ ሆኑ ሙሴ ለቀዓታውያን ሠረገሎችንም ሆነ በሬዎችን አልሰጣቸውም።
ከዚያ በኋላ ሙሴ የእግዚአብሔርን ሕግ ጽፎ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት አገልጋዮች ለሆኑት ለሌዋውያን ካህናትና ለእስራኤል ሕዝብ አለቆች ሰጣቸው።
ለሕዝቡ እንዲነግር እግዚአብሔር ኢያሱን ባዘዘው መሠረት ሁሉ ነገር እስኪፈጸም ድረስ ካህናቱ በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል እንደ ቆሙ ቈዩ፤ ሙሴም ኢያሱን ያዘዘው ይህንኑ ነበር፤ ሕዝቡም ፈጥኖ ወንዙን ተሻገሩ።
የታቦቱን ውስጣዊ ክፍል በመመልከታቸው እግዚአብሔር ተቈጥቶ ከቤት ሼሜሽ ሰዎች መካከል ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ እግዚአብሔርም ይህን ሁሉ እልቂት በመካከላቸው በማድረጉ የቤት ሼሜስ ሰዎች በማዘን አለቀሱ።