2 ሳሙኤል 15:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 ካህኑ ሳዶቅም እዚያው ነበር፤ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ሌዋውያን ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ የቃል ኪዳኑን ታቦት፥ ሕዝቡ ሁሉ ከተማውን ለቆ እስኪወጣ ድረስ በአብያታር አጠገብ አስቀመጡት። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 ሳዶቅም በዚያ ነበር፤ ዐብረውት የነበሩትም ሌዋውያን ሁሉ የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት ተሸክመው ነበር። እነርሱም የእግዚአብሔርን ታቦት ዐሳረፉ፤ አብያታርም ሕዝቡ በሙሉ ከከተማዪቱ ለቅቆ እስኪወጣ ድረስ መሥዋዕት አቀረበ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ሳዶቅም በዚያ ነበር፤ አብረውት የነበሩትም ሌዋውያን ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው መጡ፥ የእግዚአብሔርንም ታቦት፥ ሕዝቡ በሙሉ ከከተማዪቱ ለቆ እስኪ ወጣ ድረስ፥ አብያታር አጠገብ አስቀመጡ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 እነሆም፥ ደግሞ፥ ሳዶቅና ከእርሱም ጋር ሌዋውያን ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት አመጡ፤ የእግዚአብሔርንም ታቦት አስቀመጡ፤ ሕዝቡም ሁሉ ከከተማዪቱ ፈጽሞ እስኪያልፉ ድረስ አብያታር ወጣ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 እነሆም፥ ደግሞ ሳዶቅ ከእርሱም ጋር ሌዋውያን ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው መጡ፥ የእግዚአብሔርንም ታቦት አስቀመጡ፥ ሕዝቡም ሁሉ ከከተማይቱ ፈጽሞ እስኪያልፉ ድረስ አብያታር ወጣ። Ver Capítulo |