ዘኍል 34:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ወደ ዐቅራቢም መተላለፊያ ወደ ደቡብ በማምራት በጺን አልፎ እስከ ቃዴስ በርኔ ይደርሳል፤ ከዚያም በሐጻርአዳር ሰሜናዊ ምዕራብ አልፎ እስከ ዓጽሞን ይደርሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአቅረቢም መተላለፊያ አቋርጦ እስከ ጺን ይሄድና በስተ ደቡብ እስከ ቃዴስ በርኔ ይዘልቃል፤ ከዚያም በሐጸር አዳር ዐልፎ እስከ ዓጽሞን ይደርስና መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበራችሁም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ይዞራል ወደ ጺንም ይሻገራል፤ በቃዴስ በርኔ በደቡብ በኩል ያለው መጨረሻው ይሆናል፤ ወደ ሐጸርአዳር ይሄዳል ወደ ዓጽሞንም ያልፋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳርቻችሁም በአቅራቦን ዐቀበት በአዜብ በኩል ይዞራል፤ እስከ ኤናቅም ይደርሳል፤ መውጫውም በቃዴስ በርኔ በአዜብ በኩል ይሆናል፤ ወደ አራድ ሀገሮችም ይደርሳል፤ ወደ አሴሞናም ያልፋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳርቻችሁም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ይዞራል ወደ ጺንም ያልፋል፤ መውጫውም በቃዴስ በርኔ በደቡብ በኩል ይሆናል፤ ወደ ሐጸርአዳር ይሄዳል ወደ ዓጽሞንም ያልፋል፤ |
በፋራን ምድረ በዳ በቃዴስ ወደነበሩት ወደ ሙሴና አሮን ወደ መላውም የእስራኤል ማኅበር መጡ፤ እነርሱም ያዩትን ነገር ሁሉ አስረዱ፤ ያመጡትንም ፍሬ አሳዩአቸው፤
የደቡብ ድንበር ከጺን ምድረ በዳ ተነሥቶ የኤዶምን ጠረፍ እያዋሰነ ያልፋል፤ ይኸውም በስተ ምሥራቅ በኩል የሚጀምረው ከሙት ባሕር በስተ ደቡብ ጫፍ ላይ ነው።