ዘኍል 33:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዓልሞንዲ ብላታይም ተነሥተው በመጓዝ በናባው ፊት ባሉት በዓብሪም ተራራዎች ላይ ሰፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዓልሞን ዲብላታይም ተነሥተው በናባው አጠገብ በሚገኙት በዓባሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዓልሞንዲብላታይምም ተጉዘው በናባው ፊት ባሉ በዓብሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጌልሞንዲብላታይምም ተጕዘው በናባው ፊት ባሉት በአባሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዓልሞንዲብላታይምም ተጕዘው በናባው ፊት ባሉ በዓብሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ። |
“በሞአብ ምድር በኢያሪኮ ከተማ ፊት ለፊት ወደሚገኙት የዐባሪም ተራራዎች ሂድ፤ ወደ ነቦ ተራራም ውጣ፤ ከዚያም ለእስራኤል ሕዝብ የማወርሳትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት፤
ሙሴም ከሞአብ ሜዳዎች ተነሥቶ ወደ ነቦ ተራራ ወጣ፤ ከኢያሪኮም በስተምሥራቅ ወዳለው ወደ ፒስጋ ተራራ ጫፍ ደረሰ፤ ከዚያም እግዚአብሔር ምድሪቱን በሙሉ አሻግሮ እንዲመለከት አደረገው፤ ይኸውም ከገለዓድ ግዛት አንሥቶ በስተ ሰሜን በኩል እስካለው እስከ ዳን ከተማ፥