ኢዮርብዓም በይሁዳ በሚደረገው በዓል ዐይነት ስምንተኛ ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን የባዕድ አምልኮ በዓል እንዲደረግ ወሰነ፤ ከወርቅ ላሠራቸውም ምስሎች በቤትኤል በሚገኘው መሠዊያ ላይ ለጥጃ ምስሉ መሥዋዕት አቀረበ፤ በዚያም በቤትኤል ለማምለኪያ ባሠራቸው ስፍራዎች የሚያገለግሉ ካህናትን መደበ፤
ዘኍል 29:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰባተኛው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን በአንድነት ለማምለክ ትሰበሰባላችሁ፤ ይህንንም በዓል ለእግዚአብሔር ክብር በመስጠት ሰባት ቀን አክብሩ፤ በዚህም ቀን ምንም ሥራ አትሥሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በሰባተኛው ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራ አትሥሩ፤ ለእግዚአብሔርም የሰባት ቀን በዓል አክብሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰባተኛውም ወር በዓሥራ አምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፥ ሰባት ቀንም ለጌታ በዓል አድርጋችሁ ታከብራላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በሰባተኛውም ወር ዐሥራ አምስተኛዋ ቀን ለእናንተ የተቀደሰች ትሁንላችሁ፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩባት፤ ሰባት ቀንም ለእግዚአብሔር በዓል አድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰባተኛውም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፥ ሰባት ቀንም ለእግዚአብሔር በዓል አድርጉ። |
ኢዮርብዓም በይሁዳ በሚደረገው በዓል ዐይነት ስምንተኛ ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን የባዕድ አምልኮ በዓል እንዲደረግ ወሰነ፤ ከወርቅ ላሠራቸውም ምስሎች በቤትኤል በሚገኘው መሠዊያ ላይ ለጥጃ ምስሉ መሥዋዕት አቀረበ፤ በዚያም በቤትኤል ለማምለኪያ ባሠራቸው ስፍራዎች የሚያገለግሉ ካህናትን መደበ፤
እስራኤላውያን ሕጉን በሚያነቡበት ጊዜ የሰባተኛውን ወር በዓል በዳስ ውስጥ ሆነው እንዲያከብሩ መታዘዙን እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ባዘዘው ሕግ ውስጥ ተጽፎ አገኙ።
በዓሉ ከተጀመረበት ዕለት አንሥቶ እስከ መጨረሻይቱ ቀን ድረስ ዕዝራ በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ አንዳንድ ክፍል ያነብላቸው ነበር፤ በዓሉንም እስከ ሰባት ቀን አከበሩ፤ በስምንተኛውም ቀን ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት የበዓሉ መዝጊያ ሥነ ሥርዓት ተደረገ።
“የምድራችሁን ሰብል በምትሰበስቡበት ጊዜ የመከር በዓል አክብሩ፤ “ከወይን ተክሎቻችሁና ከፍራፍሬ ዛፎቻችሁ ፍሬ በምትሰበስቡበት ጊዜ በዓመቱ መጨረሻ የዳስ በዓል አክብሩ፤
“ሰባተኛው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን መከበር ለሚጀምረው የዳስ በዓል፥ መስፍኑ በሰባቱ ቀኖች በእያንዳንዱ ዕለት ለኃጢአት ስርየትና በሙሉ ለሚቃጠል ተመሳሳይ መሥዋዕት ያዘጋጃል፤ የእህሉና የዘይቱም መሥዋዕት በተመሳሳይ ሁኔታ ይቀርባል።”
በዚህ በመጀመሪያው ቀን ምንም ነውር የሌለባቸውን ዐሥራ ሦስት ወይፈኖች፥ ሁለት የበግ አውራዎች፥ አንድ ዓመት የሞላቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የምግብ ቊርባን አድርጋችሁ አቅርቡ።