ዳሩ ግን “አደጋ ለመጣል የምንጓዘው በየትኛው መንገድ ነው?” ሲል ጠየቀው። ንጉሥ ኢዮራምም “በኤዶም በረሓ የሚገኘውን ዙሪያ መንገድ ይዘን እንጓዛለን” ሲል መለሰለት።
ዘኍል 21:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን በኤዶም ግዛት ዙሪያ ለመሄድ አስበው ከሖር ተራራ ተነሥተው ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ ተጓዙ፤ ነገር ግን በመንገድ ሳሉ የሕዝቡ ትዕግሥት አለቀ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን በኤዶም ዞረው ለመሄድ ስላሰቡ ከሖር ተራራ ተነሥተው ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ ተጓዙ፤ ይሁን እንጂ ሕዝቡ በመንገድ ሳለ ትዕግሥቱ ዐለቀ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሖርም ተራራ የኤዶምያስን ምድር በዙርያው አድርገው ለመሄድ በኤርትራ ባሕር መንገድ ተጓዙ፤ ሕዝቡም በመንገድ እየተጓዙ ሳሉ ጉልበታቸው ደከመ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሖርም ተራራ በኤርትራ ባሕር መንገድ ተጓዙ፤ የኤዶምንም ምድር ዞሩአት፤ ሕዝቡም በመንገድ ተበሳጩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሖርም ተራራ ከኤዶምያስ ምድር ርቀው ሊዞሩ በኤርትራ ባሕር መንገድ ተጓዙ፤ የሕዝቡም ሰውነት ከመንገዱ የተነሣ ደከመ። |
ዳሩ ግን “አደጋ ለመጣል የምንጓዘው በየትኛው መንገድ ነው?” ሲል ጠየቀው። ንጉሥ ኢዮራምም “በኤዶም በረሓ የሚገኘውን ዙሪያ መንገድ ይዘን እንጓዛለን” ሲል መለሰለት።
ሙሴም ይህን ሁሉ ለእስራኤላውያን ነገረ፤ እነርሱ ግን በወደቀባቸው ጨካኝ ጭቈና ምክንያት መንፈሳቸው ተሰብሮ ስለ ነበረ ሊያዳምጡት አልፈለጉም።
እስከ ኤሽኮል ሸለቆ ሄደው ምድሪቱን ተመለከቱ፤ ነገር ግን ከዚያ በተመለሱ ጊዜ ሕዝቡ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ ተስፋ አስቈረጡ፤
በእነዚያም አገሮች ሁሉ አማኞች በእምነታቸው እንዲጸኑ በማበረታታትና በመምከር “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ብዙ መከራ መቀበል አለብን” እያሉ አስተማሩአቸው።
“እግዚአብሔር በነገረኝ መሠረት ወደ ምድረ በዳ ተመልሰን ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው አቅጣጫ በመጓዝ የኤዶምን ኮረብታማ ቦታ ለብዙ ቀን ዞርን።
በረሓውንም በማቋረጥ ጒዞ ቀጥለው የኤዶምንና የሞአብን ምድር በመዞር ከሞአብ በስተምሥራቅና ከአርኖን ወንዝ ባሻገር ወዳለው ስፍራ መጥተው ሰፈሩ፤ ነገር ግን የሞአብ ወሰን ስለ ነበር የአርኖንን ወንዝ አልተሻገሩም፤