ዘኍል 21:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከባሞትም ተነሥተው በሞአባውያን ግዛት ውስጥ ወዳለው ሸለቆ ተጓዙ፤ ይህም ሸለቆ የሚገኘው ከፒስጋ ተራራ ግርጌ በበረሓው ትይዩ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከባሞትም ፈስጋ ላይ ሆኖ ምድረ በዳው ቍልቍል ወደሚታይበት በሞዓብ ወደሚገኘው ሸለቆ ተጓዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከባሞትም ምድረ በዳውን ከላይ ወደሚመለከተው ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ በሞዓብ በረሀ ወዳለው ሸለቆ ተጓዙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከባሞትም ምድረ በዳውን ከላይ ወደሚመለከተው ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ በሞዓብ በረሃ ወዳለው ወደ ያኒን ሸለቆ ተጓዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከባሞትም ምድረ በዳውን ከላይ ወደሚመለከተው ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ በሞዓብ በረሀ ወዳለው ሸለቆ ተጓዙ። |
ከዚያም በፒስጋ ተራራ ጫፍ ላይ ወደሚገኘው ወደ ጾፊም መስክ ወሰደው፤ እዚያም ሰባት መሠዊያዎችን ሠርቶ በእያንዳንዱ ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ ሠዋ።
ሙሴና አልዓዛር በኢያሪኮ ትይዩ ከዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ባለው በሞአብ ሜዳ እስራኤላውያንን በቈጠሩበት ጊዜ የመዘገቡአቸው የጐሣ መሪዎች እነዚህ ነበሩ።
ይልቅስ ተነሥና ወደ ፒስጋ ተራራ ላይ ውጣ፤ በዚያም ላይ ሆነህ ዐይንህ የቻለውን ያኽል የአገሪቱን ሰሜንና ደቡብ፥ ምሥራቅና ምዕራብ አሻግረህ ተመልከት፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ መሄድ ከቶ አይፈቀድልህም።
ሙሴም ከሞአብ ሜዳዎች ተነሥቶ ወደ ነቦ ተራራ ወጣ፤ ከኢያሪኮም በስተምሥራቅ ወዳለው ወደ ፒስጋ ተራራ ጫፍ ደረሰ፤ ከዚያም እግዚአብሔር ምድሪቱን በሙሉ አሻግሮ እንዲመለከት አደረገው፤ ይኸውም ከገለዓድ ግዛት አንሥቶ በስተ ሰሜን በኩል እስካለው እስከ ዳን ከተማ፥
ይህም ምድር ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ ያለውን ግዛት ሁሉ በማጠቃለል በስተደቡብ እስከ ጨው ባሕር፥ እንዲሁም በስተምሥራቅ እስከ ፒስጋ ተራራ ግርጌ የሚደርስ ነው።