ዘኍል 21:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መኖሪያው ኔጌብ የነበረ የከነዓናውያን ንጉሥ ዐራድ እስራኤላውያን በአታሪም በኩል መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ በእነርሱ ላይ አደጋ ጥሎ ጥቂቶቹን ማረከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኔጌብ ይኖር የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ እስራኤል በአታሪም መንገድ መምጣቱን በሰማ ጊዜ በእስራኤላውያን ላይ አደጋ ጥሎ ጥቂቶቹን ማረከ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደቡብም በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ በአታሪም መንገድ እስራኤል መምጣቱን ሰማ፤ ከእስራኤልም ጋር ጦርነት አደረገ ከእርሱም ምርኮ ማረከ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአዜብ በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የአራድ ንጉሥ በአታሪን መንገድ እስራኤል እንደ መጡ ሰማ፤ ከእስራኤልም ጋር ሰልፍ አደረገ ከእነርሱም ምርኮ ማረከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደቡብም በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ በአታሪም መንገድ እስራኤል እንደ መጡ ሰማ፤ ከእስራኤልም ጋር ሰልፍ አደረገ ከእነርሱም ምርኮ ማረከ። |
የዐይ ሰዎችም ወደ ሠላሳ ስድስት ያኽል ሰዎችን ገደሉባቸው፤ ከከተማይቱ ቅጥር በር ጀምሮ እስከ ሼባሪዎ ቊልቊለት ድረስ እየገደሉ አባረሩአቸው፤ የሕዝቡም ልብ ቀልጦ እንደ ውሃ ፈሰሰ።
የሙሴ ዐማት የነበረው የቄናዊው ዘሮች ከይሁዳ ሕዝብ ጋር በመሆን የተምር ዛፎች ከሞሉባት ከኢያሪኮ ከተማ ተነሥተው፥ በይሁዳ ካለችው ከዐራድ በስተደቡብ ወዳለው ደረቅ ምድር ተጓዙ፤ እዚያም በዐማሌቃውያን መካከል ተቀመጡ።