ዘኍል 16:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በሕይወት ሳሉ ከነንብረታቸው ወደ ሙታን ዓለም ወረዱ፤ ምድርም በላያቸው ተከድና ጠፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ካላቸው ከማናቸውም ነገር ጋራ ከነሕይወታቸው ወደ መቃብር ወረዱ፤ ምድሪቱም በላያቸው ተከደነችባቸው፤ ጠፉ፤ ከማኅበረ ሰቡም ተወገዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም የእነርሱም የሆነው ሁሉ በሕይወታቸው ሳሉ ወደ ሲኦል ወረዱ፤ ምድሪቱም በእነርሱ ላይ ተዘጋችባቸው፥ ከጉባኤውም መካከል ጠፉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ ለእነርሱም የነበሩ ሁሉ በሕይወታቸው ወደ ሲኦል ወረዱ፤ ምድሪቱም ተዘጋችባቸው፤ ከማኅበሩም መካከል ጠፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ለእነርሱም የነበሩ ሁሉ በሕይወታቸው ወደ ሲኦል ወረዱ፤ ምድሪቱም ተዘጋችባቸው፥ ከጉባኤውም መካከል ጠፉ። |
እግዚአብሔር ሆይ! መንፈሴ ስለ ዛለብኝ ፈጥነህ መልስ ስጠኝ! ፊትህን ከእኔ አትሰውርብኝ! አለበለዚያ ወደ ጥልቁ ጒድጓድ እንደሚወርዱት ሰዎች እሆናለሁ።
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።
“የሙታን ዓለም የባቢሎንን ንጉሥ ለመቀበል ተዘጋጅታለች፤ የሙታን መናፍስትም ሁሉ እርሱን ለመቀበል ይንቀሳቀሳሉ፤ በምድር ላይ ኀያላን የነበሩ እጅ ይነሡታል፤ ነገሥታት የነበሩትም ከዙፋናቸው ይነሡለታል።
ከሙታን ዓለም ሊያመሰግንህ የሚችል አንድ እንኳ የለም፤ ሙታንም ሊያመሰግኑህ አይችሉም፤ ወደ መቃብር የወረዱትም ታማኝነትህን ተስፋ አያደርጉም።
የቱንም ያኽል ውሃ እየጠጣ ቢያድግ በዚህ ዐይነት ከፍተኛ ቁመት እስከ ደመና የሚደርስ ዛፍ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አይኖርም። ሟቾች በሆኑ ሰዎች ላይ የሚደርሰው የሞት ፍርድ በእነርሱም ላይ ይደርሳል፤ ወደ ሙታን ዓለምም ይወርዳሉ።”
“የሰሜን መሳፍንትና ሲዶናውያን እዚያ ናቸው፤ በሥልጣናቸው ተመክተው ሽብር ቢነዙም እንኳ ከተገደሉት ጋር በውርደት ወደ ሙታን ዓለም ወርደዋል፤ በሰይፍ ተገድለው ኀፍረታቸውን በመከናነብ ከወረዱት ጋር በእግዚአብሔር ሳያምኑ ተጋድመዋል።
በዚያ የነበሩት የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የእነዚያን ሰዎች ጩኸት በሰሙ ጊዜ ሸሹ፤ “ምድር እኛንም ልትውጠን ስለምትችል እንሩጥ!” እያሉም ጮኹ።
የአንተ አህያ ግን እኔን በማየትዋ ሦስት ጊዜ ከፊቴ ሸሸች፤ አህያይቱ እንዲህ ባታደርግ ኖሮ አንተን ገድዬ እርስዋ በሕይወት እንድትኖር በተውኳት ነበር።”
በቊጣዬ እሳት ይቀጣጠላል፤ እስከ ሲኦል ጥልቀት ድረስ ይነዳል፤ ምድርንና ምርቱን ይበላል። ቃጠሎውም እስከ ተራራዎች መሠረት ድረስ ያቃጥላል።